Blog Archives

በሊብራል ገበያ የንግድ ሥነ-ምግባር ( ጌታቸው አስፋው )

በሊብራል ገበያ የንግድ ሥነ-ምግባር *** ጌታቸው አስፋው *** በዓለም ዐቀፍ ኢኮኖሚ ጥናት ከምርትም በላይ ትኩረት ስቦ ብዙ የተባለለት ንግድ ነው፡፡ በተግባር ቅደም ተከተል ማምረት ከመነገድ ይቀድማል፡፡ ሆኖም ግን ሰዎች ከራሳቸው የግል ፍጆታ አልፈው በግብይይት መልክ ያመረቱትን ሽጠው ከገበያ የሚፈልጉትን ለመግዛት ያደረጉት እንቅስቃሴ በኢኮኖሚ ጥናት ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ የዚህ ምክንያቱም ማምረት ግላዊ ብቻ ሊሆንም ሲችል፣ ንግድ ግን ማኅበራዊ ስለሆነ ነው፣ የሰፊ ሕዝብ እንቅስቃሴ ስለሆነ ነው፡፡ ተጨማሪ እሴት የሚፈጠረው በምርት ሂደት ቢሆንም ዋጋ ግን የሚወሰነው በንግድ ሂደት ውስጥ ስለሆነ ነው፡፡ ኢኮኖሚክስ እንደ የማኅበራዊ ኑሮ ዘዴ የጥናት መስክ ሆኖ ሲጀምር የሞራልና የሥነ-ምግባር ጥበብ ነበር፡፡ ጥንት ከከፕሌቶና አሪስቶትል ጀምሮ ስለ ሀብት ይዞታና አጠቃቀም በሥነ-ምግባር ደንብ ተጠንቷል፡፡ ከኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለይ ንግድ ለብዙ ዘመናት ማጭበርበርና ማታለል ያለበት የማኅበረሰብ ጠንቅና የተወገዘ ነገር ተደርጎ ይቆጠር ነበር፡፡ ሮማውያንም የግሪኮችን ወርሰው ለንግድ በጎ አመለካከት አልነበራቸውም፡፡ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከጥሬ ገንዘብ ንግድ (ብድር) ወለድ መውሰድን እንደነውር ቆጥራ አውግዛለች፡፡ ዛሬም በእስልምና ሃይማኖት ባንክ ከሚቀመጥ ጥሬ ገንዘብ ወለድ መቀበል ሀጢዓት ተደርጎ ወለድ አይቀበሉበትም፡፡ አቅመቢሱን በንግድ ግንኙነት በዝብዞ፣ ሌላውን አደህይቶ ራስ መክበር ዛሬም ቢሆን የግለሰቦችና የአገራት የብልጽግና መንገድ ነው፡፡ ሆኖም ንግድ በሁለት ሕጋዊ ሰውነት ባላቸው አካላት ስምምነት የሚፈጸም ስለሆነ ሕጋዊ ነው፡፡ በሕግ ከተደነገጉት የሰው አካልን ወይም እጾችን ከመነገድ ሸቀጦችን ደብቆ አላግባብ እጥረት ፈጥሮ ከማትረፍ በቀር በስምምነት መነገድ ማትረፍ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News