የጸጥታ አስከባሪዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሽፋን በዜጎች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ መሆኑን የጥቃቱ ሰለባ ተናገረች።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የጸጥታ አስከባሪዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሽፋን በዜጎች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ መሆኑን የጥቃቱ ሰለባ ተናገረች። የጥቃቱ ሰለባዋ በትዊተር ገጿ እንዳሰፈረችው የፋሲካ እለት ወታደሮች ድብደባ እንደፈጸሙባትና ለሚመለከተው ባለስልጣንም ብታመለክት «የማውቀውቅልሽ ነገር የለም» ብለው ጃሮዬ ላይ ስልኩን ዘጋው። ስትል ጽፋለች ሙሉ ታሪኩን እነሆ –

—————————————

የፋሲካ ዕለት ሁሌ እንደምናደርገው ከእቶቼ ጋር walk አድርገን እየተመለስን ልክ ቅ/ማርያም ጋር ስንደርስ በመኪና ያሉ ወታደሮች”እናንተ ተራራቁ” ብለው ተቆጡን። እኛም ድንግጥ ብለን “ውይ እሺ! ግን እኮ ከአንድ ቤት ነው የወጣነው” አልናቸው።

 

ይህን እዳልናቸው በሚያስደነግጥ ፍጥነት ከመኪናቸው ዘለው ወርደው እየሮጡ ወደ እኛ መጡ የምር ሊመክሩን የመጡ ነበር የመሰለኝ! (በትህትና ማናገርም ያበሳጫል?

 

“እንዴ፣ ምን ልታደርገ ነው ስለው” አንዱ በጥፊ ሌላው በርጊጫ ሌላው ደሞ በዱላ ተረባረብብኝ! ታናናሽ እህቶቼ ደጋግመው ለመኗቸው! ግን ለእነሱ እንኳን አልራሩም፤ እነሱንም መቱዋቸው!

 

የሚሆነውን ማመን አልቻልኩም። ያለምንኩዋቸው ልመና አልነበረም! ይሄ ሁሉ ሲሆን በአካባቢው የሚያልፉ ሰዎች ነበሩ። ልክ የቀረፃ ትእይንት እንደሚያይ ሰው ገልመጥ እያደረጉ ከማለፍ ያለፈ አንድም እንኳን እባካችሁ ያለ ሰው አልነበረም።

 

ተከታታይ ዱላዎች እግሬ ላይ አረፉብኝ ። ጆሮዬ ላይ በሃይል ተመታሁ። እንደዛ ደብድበው ጥለውን ሲሄዱ ከህመሜ ባለፈ በዚህች ሀገር ላይ ጠባቂ አልባ መሆኔ፣ እንደፈለጉ እንዲያደርጉ የሚተዋቸው ህግ እንዳለ አስቤ ይበልጥ አለቀስኩ።

 

የተመታሁበት ቦታ እስከዛሬ ያመኛል። በእልህ እና በዱላው ምክንያት ሁለት ቀን በስርዓት እንቅልፍ አላገኘሁም። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ሃይ ባይ እንደሌላቸው ማመናቸው ይበልጥ አሳምሞኛል።

 

ከዩንፎርማቸው ላይ መፈራት እና ጭካኔ እንጂ በዜጎች ልብ ውስጥ የደህንነት ስሜት አለመፍጠሩ አሳዝኖኛል። (እነኛ ዝም ያሉት መንገደኞች ዝም ያሉት ጠያቂ አልባ ናቸው ብለው አይደል? ግን ያ መሆን አለበት? አይመስለኝም! )

 

ወረርሽኝን ለመከላላከል ወታደር ለምን እዳስፈለገ አልገባኝም! እነዚህ ሰዎች ምንም አይነት ተጠያቂነት የለባቸውም! የት እንደሚጠየቁ አይታወቅም! ገለውም ቢሄዱም!! እንደዚህ አይነት ጥቆማ ለመቀበል የተዘጋጀው ስልክ አይነሳም!

 

የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የሆነው ተስፋዬ ዳባ ጋር ስደውል «የማውቀውቅልሽ ነገር የለም» ብለው ጃሮዬ ላይ ስልኩን ዘጋው! ይሄ ነው ሕዝብን ማገልገል? ይሄ ነው የሕዝብ ተወካይ ማለት?

 

ማመልከቴ ለውጥ ላያመጣ ይችላል፣ ግን ደግሞ ዝም ማለት አልፈልግም። ነገ ከነገ ወዲያም እንዲህ እንዳሻቸው ያገኙትን ሰው እየደበደቡ ሊዘልቁ ነው።

 

ቢያንስ በደሉን ውጦ ዝም የማይል ሰው እንዳለ፣ ቢያንስ እነሱም ሊጠየቁ እንደሚችሉ ማወቅ አለባቸው! Ruth