#DW #HaileGebresilassie #ShashemeneResort #Ethiopia
ዶጋመድ የሆነው የኃይሌ ሻሸመኔ ሪዞርት
ከአንድ ወር በፊት በሻሸመኔ በደረሰው ከባድ ውድመት ክፉኛ ከተጎዱት ሆቴሎች መካከል የኃይሌ ሻሸመኔ ሪዞርት ተጠቃሽ ነው፡፡ በዕለቱ በዚህ ሆቴል ላይ ባነጣጠረው ጥቃት በውስጡ የሚገኙ ተሸከርካሪዎች፣ የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎችና ሙሉ ንብረቶቹ ወደ አመድነት ተቀይረዋል፡፡ የሆቴሉ ሙሉ ክፍሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶ መስኮትና በሮችም ተሰባብሮ ህንጻውን ጨምሮ በውስጡ የሚገኙ ሙሉ ንብረቶችና ሰነዶችም በቃጠሎ እንዳልነበሩ ሆነዋል፡፡ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው አስተያየት ይህኛው ባለሶስት ኮከብ ሆቴል ብዙ የተደከመበትና ከሶስት መቶ በላይ ሰራተኞችን ሲያስተዳድር የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ ሆቴሉን ወደ አገልግሎቱ ለመመለስ ከተፈለገም ሙሉ በሙሉ በማፍረስ በአዲስ መልክ መጀመር እንደሚገባ ነው የሪዞርቱ ባለቤት አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ የገለጸው፡፡
- Category
- Ethiopian News