Loading...

ሻሸመኔ መንግስታዊ ውንብድናው ቀጥሏል፤ ቤተክርስቲያን የድረሱልኝ ደውል አሰምታለች። ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ሁለት ደረሰ

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

#Ethiopia #Ethiopian #EthiopianNews #EthiopiaToday

ሻሸመኔ መንግስታዊ ውንብድናው ቀጥሏል፤ ቤተክርስቲያን የድረሱልኝ ደውል አሰምታለች። በኦሮምያ ፖሊስ ሁለት ወጣቶች ተገድለዋል::

"ምዕመናን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ለሚፈጠረው ችግር መንግሥት ኃላፊነቱን ይወስዳል"
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
++++++++++++++++++++++++++++

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾመው ቡድን መንበረ ጵጵስና እና ቤተ ክርስቲያን ሰብረን እንገባለን በማለት በምእመናን ላይ ስጋት መፍጠሩን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዲዮ፣ አማሮ፣ ቡርጂና ምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማምሻውን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን አሳወቁ።

ከሰሞኑን የሀገረ ስብከቱ አገልጋዮች ያለምክንያት እየታሰሩ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ይህንንም ለሚመለከተው የዞን ፀጥታ አካል ለማሳወቅና ጥበቃ እንዲያደርጉ ብንደውልም፣ መልእክት ብንጽፍም ሊመልሱልን አልቻሉም ብለዋል።

በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ለኦሮምያ ክልል የሚመለከታቸው አካላት በተለይም ጥበቃና ከለላን በተመለከተ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አስቀድሞ ደብዳቤ ቢጻፍም ምንም አይነት የቃልም ሆነ የተግባር መልስ እንዳልተሰጣቸውም ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም መንግሥት በሕገ ወጡ ቡድን የሚደረገውን ድርጊት ማስቆም ካልቻለ ምእመናን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ለሚፈጠረው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል ብለዋል።

በመጨረሻም ምእመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ EOTC TV

 
Category
Ethiopian News

Post your comment