Blog Archives

በቅዳሜው ሰኔ 16 ዶክተር አብይን ለመደገፍ በወጣ ሕዝብ ላይ የደረሰው የቦምብ አደጋ የአዲስ አበባ እሣትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል መምሪያ ባለሥልጣን እጁ እንዳለበት ታወቀ።

* በቅዳሜው ሰኔ 16 ዶክተር አብይን ለመደገፍ በወጣ ሕዝብ ላይ የደረሰው የቦምብ አደጋ የአዲስ አበባ እሣትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል መምሪያ ባለሥልጣን እጁ እንዳለበት ታወቀ።   * የአዲስ አበባ ፖሊስ በሸጎሌ ቀይ ሽብር የተካሄደበትን ቤት ለግድያና ለድብቅ ማሰቃያ ይጠቀምበታል የሚሉ መረጃዎች ተገኙ።   * ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ከነቤተሰቦቻቸው ወደ ሃገር ቤት እንዲገቡ የሚረዳ ንግ ግር ተጀመረ።   * በዛሬው እለት የተካሔዱ ሰልፎች በሰላም የተጠናቀቁ ሲሆን በባሕር ዳር የሚደረገው ሰልፍ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። ምንሊክ ሳልሳዊ   የአዲስ አበባ እሣትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል መምሪያ ባለሥልጣን ሃላፊዎች በሰኔ ለዶክተር አብይ ድጋፍ በተደረገው ሰልፍ ላይ ለፈነዳው ቦምብ ተባባሪ መሆናቸው መረጃ ተገኘ ፤ በዚህም መሰረት የመምሪያው ሃላፊዎች ኮማንደር አማኑኤል እረዳና ሃዲሹ ገእግዚያብሄር ሰልፉ ከመጀመሩ በፊት በመስቀል አደባባይ ቀድመው በአራቱም ማእዘናት መገኘት የነበረባቸውን አስራ ስምንት አምቡላንሶች እንዳይንቀሳቀሱ ከማገዳቸውም በተጨማሪ ከቄራ አከባቢ መምጣት የሚችሉ የእሳት አደጋ አምቡላንሶችን እንዳይንቀሳቀሱ ማገዳቸው ታውቋል ተረኛ የሆኑ ሹፌሮችንም በመበተን አንድ ሹፌር ብቻ አስቀርተው አንድ አምቡላንስ ብቻ እንዲንቀሳቀስ አዘው እንደነበር የምርመራ ውጤቱ ያሳያል።   ኮማንደር አማኑኤል እረዳ የአዲሥ አበባ እሣትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል መምሪያ ባለሥልጣን ዋና ዲሪክተር ሲሆን ሃዲሹ ገእግዚያብሄር የባለሥልጣኑ የአንቡላንሥ አሥተባባሪ ያለሙያ በዘመድ የተመደበ አጅግ አደገኛ የደሕንነት አባል መሆኑን ሰራተኞቹ ይናገራሉ። በትክክለኛው አሰራር ለህዝባዊ በአል ለሙሥሊም ለክርሥቲያን በአል ለሰልፎችም ይሁን ለሌሎች ፕሮግራሞች ከግቢ አንቡሊንሶች ወጥተው በአራት መአዘን ወተው ይቆማሉ ፤ ለአንድ ምድብ 4 አንቡላንሥ አለው።ሁሉም ሠራተኛ በተጠንቀቅ
Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News