Blog Archives

የአዲስ አበባ የባለስልጣናቱ የግድያና አፋኝ ቡድን ሲጋለጥ (ምንሊክ ሳልሳዊ)

የባለስልጣናቱ የግድያና አፋኝ ቡድን ሲጋለጥ (ምንሊክ ሳልሳዊ) የፖሊስ ባለስልጣናቱን መታሰር ተከትሎ የማሰቃያ እስር ቤቶች ስቃይ መቀነሱ ተገለጸ። የኮማንደር ግርማ ካሳን ጉዳይ ማንሳቴን ተከትሎ በውስጥ መስመር የተለያዩ መረጃዎች በተለይ ከፖሊስ አባላት ደርሰውኛል። እነሆ ተስተካክሎ ቀርቧል። ብልት ላይ የሃይላንድ ውሃ እንዲንጠለጠልና ጥፍሮች እንዲነቀሉ ትእዛዝ የሚሰጡ የፖሊስ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋል እስር ቤቶች እፎይታን አግኝተዋል። በተለይ ኮማንደር አስፋወሰን የኮሚሽነር ግርማ ካሳ ታዛዥና ታማኝ ባርያ በምርመራ ወቅት በጣም ብዙ ወገኖቻችንን እግራቸዉን በጥይት እየመታ ሽባ አድርጓቸዋል ።ሱቆችን ማቃጠል ፣ የገበያ ማእከሎችንና የግለሰቡ ሃብቶችን መዝረፍ ፣ ከሌቦች እና ማጅራት መቺ ቡድኖች ጋር በጋራ መስራት ፣ የውጪ ዜጎችን መዝረፍ ፣ በከተማዋ መኒይ ላውንደሪግ የሚሰሩ የሕወሓት ሰዎችን ከለላ መስጠት ወዘተ በርካታ የፖለቲካ የኢኮኖሚ ወንጀሎች የፈጸሙ ናቸው ፤ እነዚህ ወንጀለኛ የፖሊስ ባለስልጣናት እንዲፈቱ የሕወሓት አመራሮችና የጦር ጄኔራሎች ጫና ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። በቅዳሜው የሰኔ አስራ ስድስቱ ለዶክተር አብይ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦምብ መፈዳቱን ተከትሎ የፖሊስ ባለስልጣናት የግድያ የ አፈናና የእስር ማዘዣ ኔትወርክ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል። በተለይ ብልት ላይ የሃይላንድ ውሃ እንዲንጠለጠልና ጥፍሮች እንዲነቀሉ ትእዛዝ የሚሰጡ የፖሊስ ባለስልጣናት የሚያሰቃዩ ባለስልጣናት መታሰራቸው የተለያዩ መረጃዎች ይፋ እየሆኑ ነው። የሕወሓት አመራሮች የሚከራከሩላቸው በእስር ላይ ያሉ የፖሊስ ባለስልጣናት በቶርች ብዛት አእምሯቸውን የሳቱ ዜጎችን ከነሕይወታቸው ጫካ ውስጥና በረሐ ላይ ወስደው ለአውሬ እንደሚሰጧቸው ተጋለጠ ።በርካቶች ማንነታቸው የማይታወቅና ከተለያዩ የሐገሪይ ክፍሎች ታፍነው የመጡ ዜጎች የዚህ ቡድን ተጎጂ ናቸው።
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News