Blog Archives

ኦህዴድና ትህነግ(ሕወሓት) በማን ላይ ተስማሙ? (ጌታቸው ሺፈራው)

ኦህዴድና ትህነግ በማን ላይ ተስማሙ? (ጌታቸው ሺፈራው) ~በእነ አብይ መንግስት ላይ ግንባር ቀደሙ አማፂ ትህነግ/ህወሓት ነው። ለዚህ ስራው የቀን ጅብ የሚል ስም ተሰጥቶታል። ከወንጀሉ ሁሉ በስተጀርባ አለበት እየተባለ ነው። ዶክተር አብይ አህመድ በሚኒሶታ ለተነሳለት ጥያቄ ከአንዲት ከሁለት የትግራይ ተወላጆች የተነሳለትን ጥያቄ ከትህነግ/ህወሓት የመጣ እንደሆነ አድርጎ መልሷል። ዶክተር አብይ አህመድ በሰጠው መልስ ከትህነግ ጋር እልህ ውስጥ እንደገባ በግልፅ ያሳየ ነበር። ~ዶክተር አብይ ከአሜሪካ ከተመለሰ በኋላ በሶማሊ ክልል ለተፈፀመው ጭፍጨፋም የጅቦቹ እጅ እንዳለበት ከመገመቱ ባለፈ ፌደራል መንግስቱ በገዳዮቹ ላይ እርምጃ እንዳይወስድ በግልፅ መግለጫ የሰጠው ትህነግ ብቻ ነው። ትህነግ እንደፈለገ በሚጋልበው በሶማሊ ክልል ፕሬዝደንት ላይ የሚወሰድ እርምጃ ፌደራል ስርዓቱን እንደሚያፈርስ አድርጎ ሲያስፈራራ ቆይቷል። ~ዶክተር አብይ አህመድ እና መንግስቱ በሶማሊ ክልል ለተፈፀመው ጭካኔ የሚገባውን ሳያደርግ አልፎታል። ጭራሹን በዚህ ወቅት ዶክተር አብይ በህይወት የመኖሩ ጉዳይ ሲያጠራጥር ቆይቷል። ታፍኗል፣ ታግቷል ከማለት አልፎ በሕይወት አለ ወይ ሲባል ሰንብቶ በይፋ የታየው ደብረፅዮን ጋር ነው። ~ የግል ፀብ ያላቸው ያህል ማዶና ማዶ ሆነው አብይና ደብረፅዮን ከአብይ መጥፋት በኋላ አብረው መታየታቸው እንዲሁ የሚታይ አይደለም። በእርግጥ ዶክተር አብይ አህመድ “አንተም ተው፣ አንተ እረፍ” ብትል ከምትሰማው አሜሪካ ከርሞ ነው የመጣው። እነ ደብረፅዮን ወደ ኤርትራ ቢያንጋጥጡም ኢሳያስ “ከዛው እርጉ” ብሏቸዋል። የትህነግ እና ኦህዴድ ግብግብ የዝሆኖች ግጥሚያ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ ደብረፅዮን ከዶክተር አብይ ጋር ብቅ ብሏል ~ዶክተር አብይ አህመድ እና ደብረፅዮን አንድ ላይ የታዩት
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News