#Ethiopia #TPLF #EthiopiaArmy #Tigray #Amhara
በአሸባሪው ቁንጮ ፃድቃን ገ/ትንሣይ የሚመራው የጠላት ሀይል ፣ በሰሜን ወሎ ግንባር በተሰማራው የመከላከያ ሠራዊታችን ተመታ ።
–
ዓርሚ ሁለት የሚባልና በከሀዲው ሜ/ጄ/ል ዮሀንስ በቅፀል ስሙ ጆን ፣ በምክትሉ ከሀዲው ማዕሾ በየነ እና ከሀዲው ከበደ ፍቃዱ እንዲሁም በሜካናይዝድ አዛዡ ከሀዲው ኮ/ል ገ/ስላሴ የተመራው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ሀይል ድባቅ ተመቷል ።
–
በግንባሩ የተሰማሩ ሁለት ክ/ጦር አዛዦች እንደተናገሩት ፣ መንግስት የተናጠል የተኩሥ አቁም እርምጃውን ካነሳ በሁዋላ ከበላይ በተሠጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ጋሸናን ዋና ማዕከል በማድረግ ከዋድላ እሥከ ላሊበላ መስመር ላይ የነበረውን የአሸባሪውን ሀይል መደምሠሳቸውን አረጋግጠዋል ።
–
በአሁኑ ሰዓት ጠላት በጀግኖቹ የሠራዊት አባላት ፣ ልዩ ሀይል እንዲሁም የሚሊሻ አባላትና የአካባቢው አርሶ አደር ከበባ ውሥጥ ሆኖ ይገኛል ። ይህ የተዳከመ የጠላት ሀይል በጋሸና ፣ በመቄት ፣ በሙጃ ፣ በንፋሥ መውጫ አካባቢዎች እየተመታና እየተበተነ ይገኛል ብለዋል።
–
በነዚህ አካባቢዎች በጠላት ላይ በተደረገ ጥቃት 3 ድሽቃ ፣ 6 ሺ የድሽቃ ጥይት ፣ 87 የዕጅ ቦንብ ፣ 229 ክላሽንኮቭ ነፍስ ወከፍ መሣሪያ ፣ 5ሺ የክላሽ ጥይት ፣ አንድ የጦርሜዳ መነፅር ሢማረክ ፣ በርካታ ቁጥር ያለው የሠው ሀይል እና ጠላት ይጠቀምባቸው የነበሩ 2 መድፎች እንዲሁም አንድ ዙ 23 መደምሠሥ መቻሉን ዋና አዛዦቹ ገልፀዋል።
- Category
- Ethiopian News