Loading...

ከሁለት ዓመት በላይ በኮንቴነሮች የተከማቸ 48 ሺህ ገጀራ፣ 17 ሺህ መጥረቢያ እና 10 ሺህ ማጭድ በቁጥጥር ስር ዋለ

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

በአዲስ አበባ ከተማ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ስሙ ፋና ጣቢያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሁለት ዓመት በላይ በኮንቴነሮች ውስጥ የተከማቸ 48 ሺህ ገጀራ፣17 ሺህ መጥረቢያ እና 10 ሺህ ማጭድ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ፡፡
‹‹የተለያዩ መሣሪያዎች ፣መገልገያዎች እና አቅርቦቶች አስመጪ ድርጅት›› በሚል የንግድ ፈቃድ አማካኝነት በንግድ ስራ በሚተዳደሩት አቶ ዳርሰማ ታደሰ ህጋዊ ሂደታቸውን ሳይጠብቁ ወደ አገር ውስጥ የገቡት ቁሶች በግለሰቡ ግቢ በሚገኙ ሁለት ኮንቴነሮች ውስጥ ተከማችተው መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
መግለጫው እንዳብራራው፤ ግለሰቡ ቁሶቹን ለማስገባት ያቀረቡትን ደብዳቤ ግብርና ሚንስቴር ተቀብሎ ለሰላም ሚንሰቴር መርቶታል፡፡ ፈቃድ ሰጨው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም ከሰላም ሚንስቴር የደረሰውን የግለሰቡን ደብዳቤ ተቀብሎ ይሁንታ አልሰጠም ነበር፡፡ በዚህ መካከል ግለሰቡ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፈቃድ ሳያገኙ በ2011 ዓ.ም 48 ሺህ ገጀራ፣17 ሺህ መጥረቢያ እና 10 ሺህ ማጭድ ከውጭ አስገብተው ይውላሉ ለተባለለት አላማ ሳይሰራጩ ከሁለት አመት በላይ በግቢያቸው አክማችተውት ተግኝቷል፡፡
በግለሰቡ ግቢ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ኮንቴነሮች ውስጥ ተከማችተው የተገኙት ገጀራዎች፣መጥረቢዎችና ማጭዶች የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ባደረጉት ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋሉን ያመለከተው መግለጫው፤ ህጋዊ የንግድ ፈቃድን ሽፋን በማድረግ ለህዝብ የደህንነት ስጋት የሚፈጥሩ ህገወጥ ድርጊቶችን የሚፈፅሙ ግለሰቦችን በማጋለጥ በኩል የህብረተሰቡ ትብብር ከፍተኛ ድርሻ እንደነበረው ጠቁሟል፡፡ ዜጎች በቀጣይም አጠራጣሪ ሁኔታዎችን በአካባቢያቸው ሲመለከቱ ለጸጥታና መረጃ አካላት ጥቆማ በመስጠት ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

Category
Ethiopian News

Post your comment