Blog Archives

በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት መቅጠፉን ቀጥሏል

በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት መቅጠፉን ቀጥሏል ቢቢሲ አማርኛ ባለፉት ሁለት ሦስት ቀናት ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶች ብሄርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዲሁም የመንጋ ፍትህ ከህግ የበላይነት አንፃር ምን አይነት አደጋዎች እንደተጋረጡ አመላካች ነው። በምስራቅ ወለጋ ወሊጋልቴ ገጠር ቀበሌም ቅዳሜ እለት ማምሻውን ሁለት ግለሰቦች በቡድን በድንጋይ ተደብድበው መሞታቸው ተሰምቷል። እሁድ ደግሞ በሻሸመኔ ቦምብ ይዟል በሚል አንድ ሰውን ወጣቶች የስልክ እንጨት ላይ ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለዋል። ትላንት ጀዋር መሀመድን ለመቀበል በርካቶች በሻሸመኔ ከተማ ስታዲየም ተገኝተው ነበር። በህዝብ መጨናነቅ ሳቢያ በተከሰተው መገፋፋት ሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉም አሉ። የብዙሀኑ መነጋገሪያ የነበረው ግን ተደብዶቦ ህይወቱ ያለፈና ልብሱ ተገፎ፣ ተዘቅዝቆ የተሰቀለው ሰው ነው። ግለሰቡ ማንም ቢሆን፣ ምንም አይነት ተግባር ቢፈጽምም የደረሰበት አሰቃቂ ጥቃት ኢ-ፍትሀዊ ነው የሚሉ አስተያየቶች ተደምጠዋል። አንድን ሰው በአንድ ወንጀል ከሶ፣ ራስ ምስክር፣ ራስ ፈራጅ፣ ቀጪም ራስ የሆነበት የደቦ ፍትህ በሻሸመኔ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አካባቢዎችም እየተስተዋለ ነው። በሻሸመኔ ከተማ ጀዋርን ለመቀበል ወደ ስታዲየሙ አቅንተው ከነበሩ መካከል ስሜ አይጠቀስ ብሎ አስተያየቱን የሰጠን ግለሰብ ግርግር ካየ በኃላ ነበር ስለ ክስተቱ የሰማው። “ቦንብ ይዟል” የተባለው ሰው ተሰቅሎ የተመለከተ ሲሆን ተግባሩን “ትልቅ ስህተት” ይለዋል። ህብረተሰቡ ተረጋግቶ ማሰብና ከመሰል እርምጃ መቆጠብ እንዳለበትም ይናገራል። ሰው ተሰቅሎ ማየቱ እጅግ የዘገነነው ግለሰብ “አስጸያፊ ነው። በሀገራችን በባህላችንም የለም። ፍትሀዊም አይደደለም” ብሏል። የሻሸመኔ ከተማ የፖሊስ ኃላፊ ኮማንደር
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News