Blog Archives

በድብቅ በሚላክ ጫትና በኤርፖርት ጉምሩክ የፍተሻ ክፍተት የተነሳ ዜጎቻችን በኩዌት ለእስር እየተዳረጉ ነው

ህገወጥ ጥቅም ለማግኘት ሲባል በድብቅ በሚላክ ጫትና በኤርፖርት ጉምሩክ የፍተሻ ክፍተት የተነሳ ዜጎቻችን ለእስር እየተዳረጉ ነው ሲሉ በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቅሬታ አቀረቡ $bp("Brid_29174_1", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/07/Facebook-1993376827360850.mp4", name: "በድብቅ በሚላክ ጫትና በኤርፖርት ጉምሩክ የፍተሻ ክፍተት የተነሳ ዜጎቻችን በኩዌት ለእስር እየተዳረጉ ነው", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/07/IMG_20180702_120719.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የጫት ኦኮኖሚ (ጌታቸው በቀለ)

ከጌታቸው በቀለ የዓለም የጤና ድርጅት በ1980 ባደረገው ጥናት ጫትን ከአልኮልና ከትንባሆ ያነሰ ንጥረ ነገር የያዘ ቢሆንም፤ በአደገኛ ዕፅነት የተመዘገበ መሆኑን ያስረዳል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በርካታ አገራት ጫት ወደ አገራቸው እንዳይገባ ደንግገዋል፡፡ ይሁን እንጂ በአገራችን የጫት ተዘውታሪነት ከዕለት ወደ ዕለት እያደገ መጥቶ በለጋ ዕድሜ ያሉ ሕፃናት ሳይቀር በጫት ሱስ መያዝ በርካቶችን እያሳሰበ፣ እያወያየ የሚገኝ ርእሰ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በተለይ ከምሳ ሰዓት ጀምሮ በአገራችን ከተሞች በጫት መሸጫ ሱቆች ተኮልኩሎ፣ ጫት ገዝቶ በስስ ላስቲክ ሸክፎ ይዞ ሲሄድ የሚታየው ወጣት “አገሪቱ ወዴት እየሄደች ነው?” ያስብላል፡፡ በዘመናችን ለሰው ልጆች ከመጠን በላይ አነቃቂ ከሆኑት በርካታ ዕፀዋቶች አንዱ የኾነውን ጫት መዝገበ ቃላቱ እንደሚከተለው ይፈታዋል፤ “ለጋውን፣ ቀንበጡን…የሚያኝኩት…” ነው፡፡ (ደስታ ተክለ ወልድ፣ 1962፤ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ 629)፡፡ ጫት በሳይንሳዊ ስሙ ካታ ኤዱሊስ (Catha edulis) በመባል ይታወቃል፡፡ ጫት የየት አገር ብቃይ እንደሆነ በርካታ ጸሐፊዎች የየራሳቸውን የጥናትና ምርምር ውጤቶቻቸውን አስነብበዋል፡፡ ከተመራማሪዎቹ አንዳንዶቹ እርስ በርስ የሚቃረኑ ሐሳቦችን ቢያቀርቡም አብዛኛዎቹ ጸሐፍት ግን የጫት መገኛ አገር አቢሲኒያ (ኢትዮጵያ) እንደሆነች ይስማማሉ፡፡ (Al-habeshi and Skaug፣ 2005)፡፡ እንግሊዛዊው ጸሐፊና ተርጓሚ ሰር ሪቻርድ በርተን (Sir Richard Burton) በ1856 በጻፈው መጽሐፍ ጫት ወደ የመንና ሌሎቹ አገራት የሔደው ከኢትዮጵያ እንደሆነ ያስረዳል፡፡ (Burton፣ 1856):: በ14ኛው መ/ክ/ዘ በዐረብኛ የተጻፉ መረጃዎች፡- የምሥራቁ የአገራችን ክፍል በሆነው በሐረርጌ ደጋማ አካባቢዎች ጫት በብዛት ይመረት እንደነበርና ለየመናውያን ከ6ኛው መ/ክ/ዘ ጀምሮ መግባት መነሻ ይኸው ሐረር ነው የሚሉ የጽሑፍ
Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News