Blog Archives

በደቡብ፣ በደቡብ ምሥራቅና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ ተከስቷል

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በደቡብ፣ በደቡብ ምሥራቅና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የጎርፍ አደጋ ተከስቷል። በዚህም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ከመድረሱ ባሻገር መንገዶች በመዘጋታቸው በአካባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎች ለችግር መጋለጣቸውን ይናገራሉ። አሁን እየጣለ ያለው ዝናብ ለእርሻና ለተለያዩ ተግባራት የሚጠቀምና የተጠበቀ ቢሆንም መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ ግን የተለያዩ ጉዳቶችን እያስከተለ መሆኑን የሚናገሩት የጉጂ ዞን የአደጋ ስጋት አመራር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አበበ አባቡልጋ ናቸው። ጎርፍ ይህንን ዝናብ ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች “መንገዶች የመቆረጥ፣ ፀረ-ሰብል ተባዮች መከሰት፣ በንብረት ላይ ጥፋት መድረስና የመሳሰሉ ጉዳቶች ተከስተዋል” ይላሉ አቶ አበበ። የሚጥለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ጎርፍ ጉዳት ካደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው በባሌ ዞን መደ ወላቡ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ አህመድ ጁንዳ እንደሚሉት አደጋው የተከሰተው በዝናቡ ምክንያት ብቻ ሳይሆን በመሰረተ-ልማት ጉድለት ጭምር እንደሆነ ይጠቅሳሉ። በፌደራል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የአቅርቦትና ሎጂስቲክስ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አይድሮስ ሃሰን እንደሚሉት መንግሥት ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ላይ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን፤ ነገር ግን ከጎርፍ አደጋ ጋር በተያያዘ ከሶማሌ ክልል ውጪ ከሌሎች ቦታዎች ምንም ሪፖርት እንዳለቀረበ ይናገራሉ። የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቋቋም በአንዳንድ አካባቢዎች ቀደም ተብሎ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን የማቅረብ ሥራ እንደተከናወነ የሚናገሩት አቶ አይድሮስ “በዚህ መሰረትም በቅርበት ድጋፍ የሚሰጥ ሲሆን፤ ከዚያ በላይ ከሆነ ደግሞ በሚቀርብ ጥያቄ መሰረት ከፌደራል መንግሥቱ አስቸኳይ ምላሽ ይሰጣል።” ጨምረውም ከኦሮሚያ ክልል ከጎርፍ አደጋ ጋር ተያይዞ የቀረበ ጥያቄ እንደሌለ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News