በርግጥ የመሳፍንት ስርዓት በራሱ ከሥልጣን ሽኩቻ የዘለለ ክፋት አልነበረውም። የውጭ ወራሪ ሲመጣ የውስጥ ልዩነቱን ትቶ ጠላትን የሚያደባይ ክንደ ብርቱ ነበር። ዘመነ መሳፍንት እንደ ዛሬው ዘመነ ወራሪያን ኢትዮጵያን የሚበትን ብሄራዊ ስጋት አልነበረም። ሆኖም የኢትዮጵያ በአንድ ማዕከላዊ አስተዳድር ስር መሆን ሸጋነቱ አያጠያይቅም። ስለዚህ ስለ ላቀው የኢትዮጵያ አንድነት፣ ስለ ዘመናዊት ኢትዮጵያ ካሣ ኃይሉ ጫካ ገባ፤ ታገለ።
ታዲያ መይሰው ካሣ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጦር ሲገነባ ዳገት የሆነበት በመሳፍት ክፍፍል የተያዘው ሰራዊት ነበር። ሆኖም ጀግንነቱ፣ ቆራጥነቱ እና ሞት አይፌነቱ ሁሉንም ድል እያደረገ ርዕዩን እውን ለማድረግ አስቻለው። በመሳፍንት የተከፋፈለች ኢትዮጵያንም አንድ አደረጋት። የዚህ ወቅት የአማራ ትግልም በሕዝቡ ላይ የታወጀበትን የዘር ፍጅት አስቁሞ ህልውናውን ለማስቀጠል፣ በብሄር የተከፋፈለች ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ አንድነቷ ለመመለስ፣ ወደ መንበረ ሥልጣን ለመውጣት የቴዎድሮስን መንገድ መከተል አለበት። ለዚህም ሰሞነኛው የአማራ ልዩ ሃይል እንቅስቃሴ አጋዥ ነው።
ዘመነ ወራሪያን ኢትዮጵያን በብሄር ሰነጣጥቆ እየበተናት ይገኛል። ለመበተን የቆመቺበትን ምሰሶ መንቀል ማለትም አማራን ማጥፋት ደግሞ የሁሉም ወራሪዎች የጋራ ቀዳሚ አጀንዳ ነው። ለዚህም አማራውን ያለ ተከላካይ ለመደለቅና ለማጥፋት የአማራ ልዩ ፖሊስን ትጥቅ ማስፈታት ብሎም ከነአካቴው መበተን አስፈላጊ ሆኗል። ይህንን ተቀብሎ የጠላትን ትዕዛዝ መፈፀም ለአማራው ራስን ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ እንደመወርወር ይቆጠራል። ምርጫው ሁለት ነው፤ ወደ ገደሉ መግባት ወይም ወደ ተራራው መውጣት።
ወደ ተራራው ለመውጣት አሻፈረኝ ማለትና የአማራን ብሄራዊ ጦር ግንባታ ማጠናከር ተገቢ ነው። እያንዳዱ የአማራ ልዩ ሃይል አባል የያዘውን ጠመንጃ ለአፍታም ቢሆን