Blog Archives

የብሄር ብሄረሰብ ምሽግ ፈርሶ፣ ግልጽ አደባባይ ይገንባ!! በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር)

ሀገራዊ የስነምግባር ዝቅጠት፣ ሥርዓተ አልበኝነት፣ የፍትህ ተቋማት አቅመ ቢስነት?? ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ፣ በምንኖርበት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ስልጣኔ ታሪክ ውስጥ የሚፃፍበት ገጽ ከማይገኝላቸው ጥቂት እንስሳዊ ተግባራት አንዱ ነው፡፡ በሊባኖስ ለስልጣንና ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የበላይነት፣ እናቶችና ህፃናት ሳይቀሩ በህንፃ ፍርስራሽ ውስጥ ከእነ ህይወታቸው ይቀበራሉ፡፡ በናይናማራ ሙስሊሞች እርቃናቸውን እንደ ድንጋይ ተነጥፈው ተሽከርካሪ ይነዳባቸዋል፤ አካላቸው ይቆራረጣል፤ በረሀብ ይቀጣሉ፡፡ በኢትዮጵያ ዜጎች ከመንገድ ተይዘው ይቃጠላሉ፤ ተዘቅዝቀው ይሰቀላሉ፤ ኮበሌዎች በቢላ ይቆራረጣሉ፤ ሚሊየኖች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ከኖሩበት አካባቢ፣ ንብረታቸው እየተዘረፈ፣ ቤታቸው እየተቃጠለ፣ አካላቸው እየጎደለ ይሰደዳሉ፡፡ የኢትዮጵያውያን ግፍና ኢ-ሰብአዊ ተግባር ከሌሎች በዓለማችን ከሚደረጉት ተመሳሳይ ድርጊቶች የሚለየው ሀገራቱ በአምባገነን መሪዎች የሚመሩና መሪዎቻቸው የድርጊቱ አስፈፃሚዎች ወይም ተባባሪዎች መሆናቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያ ስለ ፍቅርና መደመር የሚዘምር፣ ስለ ዲሞክራሲና ፍትህ መከበር ሙሉ ጊዜውን የሚሰራ፣ ሀገሪቱን ከተዘፈቀችበት የጥፋት መቀመቅ ለማውጣት ቆርጦ የተነሳ መሪ ያላት፣ ግን ደግሞ ያለ መሪ ብቻ ሳይሆን፣ ያለ ህሊና በደመነፍስ ብቻ በዱር የሚኖሩ እንስሶች በዝርያዎቻቸው ላይ የማይፈጽሙት በደል የሚፈጸምባት ሀገር እየሆነች ነው፡፡ ይህቺ በሁለት እግር የሚራመዱ ፍጡራን፣ ከእንስሳዊ ደመነፍስ ሚዛን የወረደ ግፍና ጭካኔ የሚፈጽሙባት ኢትዮጵያ፣ ያለፈው ግማሽ ምእተዓመት የደርግ አምባገነንነትና የኢህአዴግ የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ናት፡፡ እነዚህ ሁለት አምባገነን መንግስታት ገድለው ይጥሉ – አስረው ያሰቃዩ ነበር። ህዝቡ ደግሞ ሲደፍር ያምጻል፤ ሲፈራ ተደብቆ ያለቅሳል፡፡  በተለይ የሃያ ሰባት ዓመት የኢህአዴግ አምባገነን አገዛዝ፣ ኢትዮጵያውያንን በጎሳ ሸንሽኖ ተፋቅረው እንዳይኖሩ፣ በጥላቻ የክልል ዋሻ ውስጥ ከትቷቸዋል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News