Blog Archives

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣዩ ሳምንት ወደ ኤርትራ በረራ ሊጀምር ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣዩ ሳምንት ወደ ኤርትራ በረራ ሊጀምር ነው። የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እንዳሉት፥ አየር መንገዱ በቀጣዩ ሳምንት ወደ ኤርትራ በረራውን ይጀምራል። በረራው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ ባደረጉት ጉብኝት ሁለቱ ሃገራት የደረሱት ስምምነት አካል መሆኑንም ተናግረዋል። ፋና
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከፍተኛ የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን የፊታችን እሁድ አስመራ ይደርሳል

የኤርትራው መርሐዬ መንግሥት ኢሳያስ አፈወርቂ ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት ከፍተኛ የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን የፊታችን እሁድ አስመራ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል ።የልዑካን ቡድኑ በዶክተር አብይ የሚመራ መሆን አለመሆኑ ማስታወቂያው አይገልፅም። በአስመራ ከተማ ለሚገኙ መምሕራን እና የመንግስት ሰራተኞች የተለጠፈው ማስታወቂያ እንዳመለከተው  ” ከአዲስ አበባ የሚመጡ እንግዶች ስላሉ እሁድ ከጠዋቱ 7፡30 ተኩል ጀምራችሁ ሁላችሁም በመንግስት ተቋማት ውስጥ የምታገለግሉ በሙሉ ወደ አስመራ ትምህርት ሚኒስትር ፅ/ቤት እንድትመጡ” የሚል መልዕክት የያዘ ነው ።  
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News