Blog Archives

በኦሮሚያ ክልል አርሲ እና ምዕራብ አርሲ አንዳንድ አካባቢዎች ሰሞኑን በባሌ ጎባ እንደተፈጠረው አይነት ግጭት ሊያስነሱ የሚችሉ ምልክቶች እየታዩ መሆናቸው ተሰማ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ እና ምዕራብ አርሲ አንዳንድ አካባቢዎች ሰሞኑን በባሌ ጎባ እንደተፈጠረው አይነት ግጭት ሊያስነሱ የሚችሉ ምልክቶች እየታዩ መሆናቸው ተሰማ፡፡ ስለዚህም የአካባቢው ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ክልሉ አሳስቧል፡፡የኦሆዴድ የገጠር ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንዳሉት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን እና ምዕራብ ዞን እንደ ባሌ ጎባው አይነት ግጭት ሊያስከትሉ የሚችሉ ምልክቶች ታይተዋል፡፡ ስለዚህም የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ቄሮ እና በየአካባቢው ያሉ የስራ ሀላፊዎች የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ባሌ ጎባ በተፈጠረ አለመግባባት በተነሳው ግጭት የ10 ሰዎች ሕይወት ማለፉና በርካቶች መቁሰላቸው ይታወሳል፡፡በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ለግጭት መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ ስለተባሉት ምልክቶች ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ክልሉ ኮሚኒኬሽን ሀላፊዎች ስልክ ብንደውልም የሀላፊዎቹ ስልክ አይነሳም፡፡ source – sheger fm
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News