Blog Archives

ባሌ ጎባዎች እርቀ ሰላም አውርደዋል !

ባሌ ጎባዎች እርቀ ሰላም አውርደዋል ! ህዝቡና በወይዘሮ አዳነች አቤቤ የተመራው የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ፈተውታል ! ገለቶማ !!!
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኦሮሚያ ክልል አርሲ እና ምዕራብ አርሲ አንዳንድ አካባቢዎች ሰሞኑን በባሌ ጎባ እንደተፈጠረው አይነት ግጭት ሊያስነሱ የሚችሉ ምልክቶች እየታዩ መሆናቸው ተሰማ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ እና ምዕራብ አርሲ አንዳንድ አካባቢዎች ሰሞኑን በባሌ ጎባ እንደተፈጠረው አይነት ግጭት ሊያስነሱ የሚችሉ ምልክቶች እየታዩ መሆናቸው ተሰማ፡፡ ስለዚህም የአካባቢው ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ክልሉ አሳስቧል፡፡የኦሆዴድ የገጠር ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንዳሉት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን እና ምዕራብ ዞን እንደ ባሌ ጎባው አይነት ግጭት ሊያስከትሉ የሚችሉ ምልክቶች ታይተዋል፡፡ ስለዚህም የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ቄሮ እና በየአካባቢው ያሉ የስራ ሀላፊዎች የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ባሌ ጎባ በተፈጠረ አለመግባባት በተነሳው ግጭት የ10 ሰዎች ሕይወት ማለፉና በርካቶች መቁሰላቸው ይታወሳል፡፡በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ለግጭት መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ ስለተባሉት ምልክቶች ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ክልሉ ኮሚኒኬሽን ሀላፊዎች ስልክ ብንደውልም የሀላፊዎቹ ስልክ አይነሳም፡፡ source – sheger fm
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከባሌ ጎባ ከተማ ግጭት ጋር በተያያዘ 35 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

  ከባሌ ጎባ ከተማ ግጭት ጋር በተያያዘ 35 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ $bp("Brid_37036_1", {"id":"12272", "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/07/Facebook-2033432100021989.mp4", name: "ከባሌ ጎባ ከተማ ግጭት ጋር በተያያዘ 35 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/07/FB_IMG_1532258994463.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በባሌ ጎባ ግጭት ጀርባ የወያኔ ደህንነቶች እጅ መኖሩ ተገለፀ።

ከባሌ ጎባ ግጭት ጀርባ ያሉ እጆች ከጀዋር መሀመድ ስለባሌ ጎባ ግጭት በአፋን ኦሮሞ ከለጠፈው የተተረጎመ (ኦሮሚኛው ከታች ይገኛል) “ባሌ ጎባ ላይ ዛሬም አመፁ ቀጥሎዋል። ሶስት ሰው ነው የተገደለው። ችግሩ በፍፁም የሃይማኖት ጉዳይ እንደሌለበት ተረጋግጦዋል። ቄሮዎቹ በሃይማኖት ሳይከፋፈሉ ሐውልቱን ለማቆም ነበር የተንቀሳቀሱት። ደህንነት የነበሩ ሰዎች ናቸው አማረ በሚኖርበት ሰፈር ተቀምጠው በመተኮስ ሕዝብ እያጋጩ ያሉት። የዚህ ተንኮል ጠንሳሾችና አቀናባሪዎችም፦ 1. ደጃን፣ የወያኔ ደህንነት 2. አሸናፊ ወ/ዮሐንስ፣ ቄሮን ሲያሳድድ የነበረና የሰዌና ወረዳ ፖሊስ የኦሮሞ ሕዝብ መከታ እንዳይሆን እንቅፋት የሆነ። 3. አወል ሐሰን የሰዌና ወረዳ አስተዳዳሪ የነበረና አሁን የጎባ ወረዳ ደህንነት ኃላፊ የሆነ። ሕዝባችን፣ አማረና ኦሮሞ ይህን አውቆ ነገሩን በማረጋጋት ያለውን ልዩነት በውይይት መፍታት አለበት።” ጀዋር ሙሐመድ በአፋን ኦሮሞ ከለጠፈው የተተረጎመ በምንሊክ ሳልሳዊ Goobatti jeequmsi har’as itti fufee jira. Nama sadihitu ajjeefame. Dubbiin dhimma amantii gonkumaa akka of keessaa hin qabne mirkanaayee jira. Qeerroon amantiin osoo wal hin qoodin siidaa san jaaruuf socho’an. Warra dehinantii turetu safara saba Amaaraa keessa taa’ee dhukaasee ummata walitti buusaa jira. Shira kana kan qindeessaa jiran 1)Dajan (human tikaa waayyaanee) 2)Ashannaafii W/Yohaannis nama qeerroo adamsaa turee fi poolisii aanaa sawweenaa akka gaachan ummata oromoo him taane godhaa ture. 3)Awwal Hassan (bulchaa aanaa sawweenaa kan turee fi alma I/G nageenyaa aanaa Goobbaa kan ta’eedha.) Ummanni keenya Amaaraafi Oromoo kana beekuun
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የባሌ ጎባው ግጭት ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን ለማጋጨት የተጠነሰስ እኩይ ሥራ ነው ተባለ።

የግጭቱ መነሻ “ቀይ ቀበሮ አደባባይ” የተሰኘውን አደባባይ “ሃጂ አደም ሳዶ” አደባባይ ብለን እንቀይረዋለን በሚሉ ከጎባ ከተማ ውጭ በመጡ ወጣቶችና በከተማው ሕዝብ መካከል የተፈጠረ አለመግባባት ነው። *** ቦታው ታቦታት የሚያርፉበትና የሚያልፉበት መሆኑ እየታወቀ የሙስሊም አማኝ በሆኑ ግለሰብ ስም እንዲሰየም ማድረግ ሆነ ተብሎ ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን ለማጋጨት የተጠነሰስ እኩይ ሥራ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው የጎባ መምህር። *** አለመግባባቱም ቀስ በቀስ ሃይማኖታዊ መልክ እየያዘ በመምጣት ወደ ግጭት አምርቶ የሰዎች ሕይወት ጠፍትዋል። አሁንም በጣም አስፈሪ መልክ እየያዘ እንደቀጠለ ነው። *** እስካሁን የሁለት ክርስቲያን እና የአንድ ሙስሊም አስክሬን ከጎባ ሆስፒታል ወጥቶ ለሕዝቡ ተሰጥቷል። ሕዝቡም በአንድ ላይ በመሆን ሙስሊሙን በሙስሊም መቃብር ካሳረፈ በሁዋላ የካሱ እና በረከት (ማንዴላ) የተባሉ ክርስቲያኖችን አስክሬን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ቀብርዋል። *** ግጭቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው። እየተከታተልን እንገልጽላችሁዋለን። Muluken Tesfaw
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook