Blog Archives

ከአንድ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተናጋሪ ያላቸውን ቋንቋዎች የፌደራል የሥራ ቋንቋ ማድረግ፤ በክልሎች ያለውን የቋንቋ አፓርታይድ መስበር። (ኒሻን በላይ)

ከአንድ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተናጋሪ ያላቸውን ቋንቋዎች የፌደራል የሥራ ቋንቋ ማድረግ፤ በክልሎች ያለውን የቋንቋ አፓርታይድ መስበር። *** ኒሻን በላይ *** የጽሑፌ ጭብጥ፡- በአገራችን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተናጋሪ ያላቸው ቋንቋዎች የፌደራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ እና በክልሎች ሰፍኖ የሚገኘው የቋንቋ ምስቅልቅል እንዲሻሻል ያስፈልጋል የሚል ነው፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ ስለቋንቋ ሕግና ፖሊሲ ስንነጋገር፣ የሕጉና ፖሊሲው ተቀዳሚ ዓላማ ዜጎች በራሳቸው ቋንቋ የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብት ያላቸው መሆኑን ተቀብሎ ይህንን መብት ማስጠበቅ ነው፡፡ በሌላ በኩል፣ ቋንቋ በሚመለከት የሚወጡ ሕጎችና ፖሊሲዎች የብሔረ መንግሥት ግንባታውን (nation building) በሚያግዝ መልኩ የተቃኙ እንዲሆኑ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም ቋንቋን አስመልክተው የሚወጡ ሕጎችና ፖሊሲዎች ከጊዜያዊ የፖለቲካ ሆይሆይታ በፀዳ መልኩ በሰከነ፣ በተጠናና ሕዝብን ባሳተፈ መልኩ ሊዘጋጁ ይገባል፡፡ ጥናት፣ ውይይት እና ክርክር ይቅደሙ፡፡ አርቆ-ማሰብ የሚጠይቅ ግዙፍ አጀንዳ ስለሆነ ሰከን ብለን እንያዘው፡፡ በእኔ አስተያየት፣ በአገራችን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተናጋሪ ያላቸውን ቋንቋዎች የፌደራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ ማድረግ ከፍ ያለ ጠቀሜታ አለው፡፡ ጉዳዩን ከብሔረ መንግሥት ግንባታ አንጻር ብንመለከተው፣ ለምሳሌ ሶማልኛ ቋንቋ የፌደራል መንግሥቱ የሥራ ቋንቋ መሆኑ፣ የሶማሊ ብሔር አባላት በፌደራል ደረጃ በራሳቸው ቋንቋ የመጠቀም መብታቸውን ከመጨመሩም በላይ፣ በሶማሊ ብሔር አባላት ላይ የሚፈጥረው ስሜት በጣም ከፍተኛ እንደሚሆን የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ ይህ ስሜት በትግራይ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ፣ ሲዳማ እና ሌሎች ብሔሮች ላይም እንደሚኖር መገንዘብ አይከብደም፡፡ ይህ ስሜት ነው ሁሉንም ባይባል ከፍ ከፍ ያለ ቁጥር ያላቸው ብሔሮች በተቀራራቢ ደረጃ ለአገሪቱ ህልውና መጠበቅና ሁለንተናዊ ልማት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News