Blog Archives

እየታየ ያለውን ለውጥ እንዴት እንጠቀምበት? – ብርሃኑ አበጋዝ

ዶ/ር ብርሃኑ አበጋዝ – አዲስ አበባ ሽግግር ላይ ነን፡፡ አብዮታዊ ሊባሉ የሚችሉ እርምጃዎች እየተወሰዱ፣ በርካታ አገርና ሕዝብ ሊጠቅሙ የሚችሉ ውሳኔዎችም እየተላለፉ ነው፡፡ ይህ ሒደት ፍጻሜው ያማረ እንዲሆን መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ ለውጡ ዴሞክራሲን በሚያዋልድ መልኩ ፍጻሜ እንዲያገኝ ማድረግ ይገባል፡፡ ዋናውና ትልቁ ፈተና ኢትዮጵያዊያን ለፖለቲካ ሽግግር አዲስ መሆናችን ነው፤ እንግዳ ነን፡፡ ግልጽ መሆን ያለበት፣ በታሪካችን ፖለቲካ ጅማሮ እያሳየ ያለው አሁን ነው፡፡ ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ምሁራን የሚፈተኑበት ጊዜም አሁን ነው፡፡ ምን ያህል ዝግጁ ነን? የፖለቲካ ልሂቃኑ ይህ ለውጥ አገርና ወገን በሚጠቅም መልኩ እንዲቀጥል ምን ያህል ዝግጁነት አላቸው? የታሪክ ጥያቄ አለ፤ የፍትሕ ጥያቄ አለ፤ የዴሞክራሲ አለ፤ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጥያቄ አለ፡፡ ሌሎችም ብዙ ጥያቄዎች አሉ፤ የተለያዩ፣ እንዳንዴም የሚጋጩ የፖለቲካ ፍላጎቶች ያሏቸው በርካታ የፖለቲካ ኀይሎችም አሉ፡፡ አፍጥጠው የመጡት የሚጋጩ ፍላጎቶች ሊስተናገዱ የሚችሉባቸው ተቋማት ግን የሉንም፡፡ ሥርዓታት (institutions) አልገነባንም፡፡ ትልቁ ፈተናም ይህ ነው፡፡ ሥርዓታትና ተቋማት በሌሉበት ሁኔታ የሚደረግ የፖለቲካ ውድድር (political contestation) ፍሬው ያማረ አይሆንም፡፡ አገርና ሕዝብ ከፖለቲካ ኀይሎች ውድድር ሊጠቀሙ የሚችሉት ውድድሩን ሊያስተናግድ የሚችል መጫዎቻ ሜዳና ጨዋታውን በእኩል መንገድ የሚያስተናገድ ሥርዓት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ እንዲህ ካልሆነ ለውጡ በተደራጁ ኀይሎች እጅ ገብቶ ሊኮላሽና ተመልሰን ወደ አፈና ሥርዓት ልንገባ የምንችልበት ሰፊ ዕድል አለ፡፡ ልክ የግብጽ አብዮተኞች በ2002 ዓ.ም. ማግስት እንገጠመቻውና የማታ ማታ አገሪቱም ተመልሳ በአምባገነነናዊ ሥርዓት መዳፍ ሥር እንደገባችው፡፡ የዚህ ዓይነቱ መዘዘኛ ቅልበሳ እንዳይመጣና ሁላችንም ተስፋ ያደረግንበት ለውጥ ወደ ዴሞክራሲ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News