Blog Archives

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች ሲከናወኑ መቆየቱን ኢሶህዴፓ አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች ሲከናወኑ መቆየቱን የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶህዴፓ/ አስታውቋል፡፡ ኢሶህዴፓ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በላከው መግለጫ የኪራይ ሰብሳቢነት እና የሙስና መንሰራፋት የክልሉን ህዝብ በመልካም አስተዳደር እጦት እንዲሰቃይ አድርጎታል ብሏል፡፡ የብልሹ አሰራር ስር መስደድ፤ የአመራር መምከን እና ወደ ገዥ መደብነት መቀየር ስር የሰደዱ የፓርቲው ችግር መሆናቸውን አስታውቋል፡፡ በመሆኑም የችግሩ ባለቤት የአሶዴህፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ በመሆኑ በወሰደው እርምጃ 3 የኢሶህዴፓ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እና 5 የማእከላዊ ኮሚቴ አመራሮች ከኮሚቴዎቹ እንዲታገዱ ተወስኗል፡፡ ከኢሶህዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ የተሰጠውን ድርጅታዊ ሙሉ መግለጫ ያንበቡ የኢሶህዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አሁን በሀገራችን እና በኢትዮጵያ ሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ካለው የለውጥ ሂደት እና ጊዜው ከሚጠይቀው ድርጅታዊ ቁመና ጋር የሚሰምር ሁሉን አቀፍ ማስተካከያ ማድረግ ይቻል ዘንድ ከነሀሴ 4 እስከ ነሀሴ 11 ቀን 2010 ዓ.ም ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት ግምገማ ሲያካሂድ ቆይቶ ውጤታማ የሆኑ ውሳኔዎችን እና በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎችም ምቹ መደላድል የሚፈጥሩ ውይይቶችን በማድረግ በስኬት ተጠናቋል፡፡ ኢሶህዴፓ ባካሄደው በዚህ ታሪካዊ ግምገማ ወቅት ትኩረት ሰጥቶ ከገመገማቸው አንኳር ጉዳዮች ውስጥ ፓርቲው አሁን የሚገኝበትን እና በተራዛሚውም ሂደት ኢሶህዴፓ እያስተዳደረ ያለው የኢትዮጵያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ የተዳሰሰበት በሳል ግምገማ በዋነኝነት ይጠቀሳል፡ በዚህ ግምገማ ሂደትም የሶማሌ ክልል ህዝብን በተጨባጭ እየተገዳደሩ የሚገኙ እና ከልማት እና ከመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ረገድ እንቅፋት እየሆኑ ያሉ ተግዳሮቶችን ከነዝርዝር መገለጫቸው፣ ምንነታቸው እና ምንጫቸው ጭምር በመገምገም
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News