ፖለቲከኛ ሀብታሙ አያሌው – በነጻነት ማግስት
የልቤን ምጥ ልፃፈው ብዬ ደጋግሜ ብዕሬን ይዤ ወረቀቱ ላይ ብፅፍም እንደተራበው ወገኔ ሆድ ብዕሬ ባዶ ሆኖ ቀለም አልነጥበው አለ፡፡ በቅሊንጦ ማጎሪያ ቤት ሰማይ ስር ነፍሴ ሀዘን አቆርዝዛ በማይገፉ ቀንና ሌሊቶች ውስጥ ባዘነች፡፡ ለወትሮው ወገኔ እንደከፋው ስሰማ እንደወፍ በርሬ ችግሩን ልጋራው
…
ወንድማችን ሃብታሙ አያሌዉ በጠና ታሞ ትናንት ምሽት ዘዉዲቱ ሆስፒታል ለህክምና ገብቷል፡፡የህመሙ ምክንያት ለቤተሰቡ ያልተገለጸ ሲሆን ባለቤቱም ገብታ እንድትጥቀዉ ያልተፈቀደላት መሆኑን (እንባ ባላባሩት አይኖችዋ ዘለላዎችን እያፈሰሰች በለቅሶ ታጅባ) ትናገራለች፡፡ሰሞኑን በሙሉ ጤና እንደነበር ቂሊንጦ እስር ቤት ሄደዉ የጠየቁት ጎዶች ይናገራሉ፡፡