Blog Archives

የበርካቶች ሕይወት በጠፋበት የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ በአካል ከነበሩ ጋዜጠኞች ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ – VOA


በትናንትናው ዕለት በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሃይቅ ለመከበር በዝግጅት ላይ የነበረውና ከኦሮሞ ክብረ በዓሎች አንዱ የሆነው ኢሬቻ በዓል ላይ ለዘገባ ተገኝተው የነበሩ ጋዜጠኞች የተከታተሉትን በዝርዝር ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ጽዮን ግርማ የተወሰኑትን አነጋግራ ተከታዩን አጠናቅራለች። ያድምጡ ↓

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

የኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ጉዳይ የሚታየው ጎንደር ላይ ነው – VOA

colonel-demeke-zewde
የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ተጨማሪ የሽብር ምርመራ በፌደራል ፖሊስ ሊካሄድባቸው የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቋል፡፡ ኮ/ል ደመቀ አሁንም ክሥ ያልተመሠረተባቸው ሲሆን ጉዳያቸው ከትናንት በስተያ፤ መስከረም 18/2009 ዓ.ም የታየው በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት …

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከረፍት መልስ – VOA

Dilla University
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ዲግሪ በተለያየ ሙያ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እረፍታቸውን ጨርሰው የ2009 የትምህርት ዘመን ለመጀመር ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ወደየ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ። ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ → listen

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

ከኦህዴድ ሹም ሽር ጋር በተያያዘ ከዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ – VOA


የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ነበሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በመንግሥት የሥልጣን አመራር ዘመናቸውም የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) የፓርቲ አባልና ሥራ አስፈጻሚ አባልና ከፍተኛ አመራር ነበሩ። በኦህዴድ ውስጥ የተደረገው ሹም ሹር ምን እንደምታ እንዳለው አስተያየር እንዲሰጡ ተጠይቀዋል። ጽዮን ግርማ አነጋግራቸዋለች → LISTEN

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

“የፀጥታ ኃይሎች የሚተኩሱት ሕዝብ ላይ ነው” አቶ አዳነ ጥላሁን – VOA

tplf-agazi-soldiers-carry-out-shoot-to-kill-order-against-peaceful-protesters
የፀጥታ ኃይሎች ጨዋ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ይተኩሳሉ፣ ይገድላሉ ያሉት ተቃዋሚዎች ተጠያቂዎቹም የመንግሥት የፖለቲካ መሪዎች እንደሆኑ አስታውቀዋል። ዘገባውን ያዳምጡ → listen

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

ቁጥሩ እጅግ የበዛ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፈኛ በዋሽንግተን የተቃውሞ ድምጹን ሲያሰማ ዋለ – VOA

ከዋሽንግተን ዲሲና ከአካባቢው እንዲሁም ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የመጡ ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ በዋይት ሃውስ እና በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ደጃፎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።

ሕጻናት የያዙ እናቶችና አዛውንቶች ጭምር የነበሩበት እጅግ የበዛ ቁጥር ያለው …

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

በነቀምት የወታደር ካምፕ ላይ ቦንብ ከፈነዳ በኋላ ከተማው ውጥረት ላይ መሆኑን ተገለጸ – VOA

Nekempte, western Ethiopia
በትናንትናው ዕለት በነቀምት ከተማ ደርጊ ወይም ቀበሌ ሁለት በተባለ ቦታ ባልታወቁ ሰዎች በኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮች ካምፕ ላይ የፈነዳ ቦምብ ጉዳት ማድረሱ ተገለጿል። ከጉዳቱ በኋላ በአካባቢው የተገኘው ሰው ሁሉ ድብደባ ደርሶበታል ሲሉ ነዋሪዎች ያማርራሉ። ዘገባውን ያዳምጡ → listen

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

በምዕራብ አማራ የተለያዩ አካባቢዎች እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው – VOA


በጎንደር፣ በአዴት፣ በዳንግላና ሌሎችም ሥፍራዎች የታሠሩ ሰዎች መኖራቸውንና የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ ዋና ፀሐፊም እየተፈለጉ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ ስለሁኔታው መረጃ እንደሌላቸው የኮሚቴው ዋና ፀሐፊ አቶ ተሻገር የሚሠሩበት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፀጥታና የደኅንነት ኃላፊ አመልክተዋል፡፡

እንዲሁም ዳንግላ ላይ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ – …

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

አጣብቂኝ ውስጥ የገባች አገር ጉዳይ፥ ሰሞንኛ ይዞታዋና ተሥፋዎቿ – VOA

Mesfin Woldemariam
የአገር ፈተናዎች፥ የመውጫ መንገዶችና ተሥፋ፤ አንጋፋው የኢትዮጵያ ጉዳይ አዋቂ፥ ደራሲና የመብት ተሟጋች ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማሪያም ትላንትናችንን፥ ዛሬንና ነገን፤ መንታ መንገድ ላይ ያለች በምትመስለው ሃገር ሰሞንኛ ይዞታ ውስጥ ይቃኛሉ → listen

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

የሰሞኑ የበዓል ገበያ ቅኝት – VOA

Merkato, Addis Ababa
ያዳምጡ → listen

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክርቤት ሰብሳቢ በቁጥጥር ሥር ዋሉ – VOA

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

የሆሳዕና እስረኞች ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ገለጹ


በኢትዮጵያ ደቡብ ህዝቦች ክልል ሆሳዕና በሚገኝ እስር ቤት ካለፈው ዕሁድ ጀምሮ የመንግስት ሓይሎች በእስረኞች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ከእስረኞች አንዱ ገለጹ። Listen

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

በምዕራብ ሃረርጌ መሰላ ወረዳ የፀጥታ ኃይሎች ወሰዱ በተባሉ እርምጃዎች ሕይወት ጠፍቷል – VOA


በምዕራብ ሃረርጌ መሰላ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ሰሞኑን የፀጥታ ኃይሎች ወሰዱ በተባሉ እርምጃዎች ሁለት ሰው መገደሉን የወረዳው አስተዳዳሪ ገልፀዋል፡፡ ዝርዝሩን ያዳምጡ → listen

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

በጎንደር ከተማ በተቀሰቀ ግጭት የሰው ሕይወት ጠፋ – VOA

በዛሬው ዕለት በጎንደር ከተማ በተቀሰቀ ግጭት የሰው ሕይወት ጠፋ። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እስካሁን የአራት ሰው ሕይወት ጠፍቷል ሲሉ የክልሉ መንግሥት እስካሁን ባለን መረጃ የጠፋው የአንድ ሰው ሕይወት ነው ብሏል። ዘገባውን ያዳምጡ → listen

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

ነዋሪዎች ስለ ዛሬው የጎንደር ውሎ ይናገራሉ – VOA


ሐምሌ አራት ለሐምሌ አምስት አጥቢያ የፌደራል ልብስ ለብሰው ጭንብል ያጠለቁና ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማነንት ጥያቄ ኮሚቴ አራት አባላትን አፍነው በመውሰዳቸና፤ አንዱን የኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በግዳጅ ለመውሰድ በተደረገ ግብግብ በጎንደር ከተማ ግጭት መጫሩ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን …

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

በፌስቡክ ምክንያት በርካታ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ – VOA


ከረጅም ዓመታት በፊት በፖለቲካ ምክንያት በሶማሊያ መኖር እንዳልቻሉ በመግለጽ በኖርዌይ ያቀረቡት የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይንት አግኝቶ ፤ የመኖሪያ ፈቃድ እና ዜግነንት ተሰጥቷቸው የነበሩ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ። ለዚህ ሁሉ የዳረጋቸው ደግሞ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ስለራሳቸው የሚያወጡት መረጃ …

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

አትሌት ኩለኒ ገልቻ በወንድ ጓደኛዋ ተወግታ ተገደለች – VOA

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ ውስጥ በመካከለኛ ርቀት 800 ሜትር ተወዳዳሪ የነበረችውና በብሔራዊ ቡድን ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ተመራጭ በመሆን የምትታወቀው የ19 አመትዋ አትሌት ኩለኒ ገልቻ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በአትሌት ጓደኛዋ እጅ ህይወቷ በስለት ማለፉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፌዴራል …

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ጥቃት ያደረስኩት እኔ ነኝ ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ኃላፊነቱን ወስዷል – VOA

Arba Minch
ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ጥቃት ያደረስኩት እኔ ነኝ ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ኃላፊነቱን ወስዷል። የድርጅቱ ሊቀ መንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ፥ ”ትግላችንን የምናካሂደው እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሆነን ነው” ብለዋል። ያዳምጡ → listen

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

በያቤሎ የአውቶቡስ አደጋ አሥራ ሦስት ሰው ሞተ – VOA

በደቡብ ኦሮምያ፤ ቦረና ዞን ውስጥ ትናንት፣ ዓርብ ምሽት ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ ቢያንስ የ13 ሰው ሕይወት መጥፋቱን የሆስፒታል ምንጮች አስታወቁ፡፡

አደጋው የደረሰው አንድ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከልክ በላይ አሳፍሮ ሜጋ ወረዳ ውስጥ ካለችው የዓርብ ገበያ ከሚቆምባት ዱቡሉቂ ከተማ ወደ …

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

በምዕራብ ወለጋ ዞን ከፖሊስ ድብደባ ጋር በተያያዘ አንድ ተማሪ መሞቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ይገልጻሉ – VOA

በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ ውስጥ ባለፈው ዕሁድ ሌሊት ከፖሊስ ድብደባ ጋር በተያያዘ አንድ ተማሪ መሞቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ለኦሮምኛ ፕሮግራም ክፍል ባልደረባ ለጃለኔ ገመዳ ተናግረዋል። የነጆ ከተማ አስተዳደር ግን ተማሪው የሞተው በሕመም ምክንያት መሆኑን ሐኪም አረጋግጧል ይላል። ​በሌላ በኩል፥ ቤተሰብ …

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት አፈናው ተባብሷል – የጥናት ባለሞያዎች (VOA)

“በኢትዮጵያ ያለው የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ምን ይመስላል?” ስትል ጽዮን ግርማ የሂዩማን ራይትስ ዎች የጥናት ባለሞያ ፍሊክስ ሆርንና የደህንነት ጥናት ተቋም የጥናትና ምርምር ባለሞያ ሃሌሉያ ሉሌን ጠይቃለች። ሁለቱም ባለሞያዎች በኢትዮያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት እጦት ተባብሷል ይላሉ። ሙሉ ዘገባውን ያዳምጡ → listen

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

33 ሰዎች የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ድርጅታዊ ህዋስ በመመሥረትና በአሸባሪነት ተከሰሱ – VOA

Ethiopian Federal Supreme Court
የኢትዮጵያው ፌዴራል ዐቃቤ ህግ 33 ሰዎችን በአገር ውስጥ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን (የኦነግን) ድርጅታዊ ህዋስ በመመሥረት፣ በመምራትና አባላት በመሆን የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል ሲል በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ መሠረተባቸው። ፍርድ ቤቱም፣ ተከሳሾቹ መልስ እንዲሰጡ በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ …

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

የኦፌኮ ከፍተኛ የአመራር አባላት በማረሚያ ቤት ከፍተኛ በደል ይደርስብናል አሉ – VOA

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ የአመራር አባል አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 በሽብር የተጠረጠሩ ተከሳሾች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀረቡ። እነ አቶ በቀለ በማረሚያ ቤት ስድብ ማስፈራራትና ሌሎችም ከፍተኛ ተጽኖዎች እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ …

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

የቆሎ ተማሪ በአሜሪካ – VOA

የኢትዮጵያን ቋንቋ፣ ታሪክና ባህል ለበርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዳጊ ህፃናትንና ወጣቶችን በማስተማር ላይ ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት መካከል በሜሪላንድ የሚገኘው የደብረ ገነት መድሃኒያለም ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አንዱ ነው። በዚሁ ቤተክርስቲያን በምክትል አስተዳዳሪነትና በቅዳሴ በማገልገል ላይ የሚገኙት መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ገብረወልድ አገዝ ወደ …

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news

በትግራይ የእምባስነይቲ ህዝብ ቅሬታውን በሰልፍ ገለፀ – VOA


በትግራይ ክልል የእምባስነይቲ ህዝብ ቀድሞ የነበረውን ወረዳ እንዲመለስለት ከ20 ዓመታት በላይ ጠይቆ አወንታዊ መልስ ባለማግኘቱ ምክንያት የተሰማውን ቅሬታ ትላንት በሰላማዊ ሰልፍ ገልጿል። መንግስት የቆየውን ወረዳችን የማይመልስልን ከሆነ ከወረዳ እስከ ተወካዮች ምክር ቤት የወከልናቸውን ሰዎች ከዛሬ ጀምሮ ውክልናችን ማንሳታችን እንገልፃለን ብሏል …

Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian news