የኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ጉዳይ የሚታየው ጎንደር ላይ ነው – VOA


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


colonel-demeke-zewde
የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ተጨማሪ የሽብር ምርመራ በፌደራል ፖሊስ ሊካሄድባቸው የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቋል፡፡ ኮ/ል ደመቀ አሁንም ክሥ ያልተመሠረተባቸው ሲሆን ጉዳያቸው ከትናንት በስተያ፤ መስከረም 18/2009 ዓ.ም የታየው በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት መሆኑን ጠበቃቸው አቶ መክት ካሣሁን ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

በግድያ ወንጀል የጠረጠራቸው ፖሊስ የምርመራ መዝገብ በዕለቱ ተዘግቶ አቃቤ ሕግ ክሥ ይመሠርት ወይም ሌላ ሃሣብ ያቀርብ እንደሆነ የ15 ቀናት ጊዜ ያለው መሆኑን አቶ መክት ገልፀው አዲስ ለተከፈተው ምርመራ ፖሊስ የሃያ ስምንት ቀን ቀጠሮ ጠይቆ እንደነበር አመልክተዋል፡፡ እርሣቸውና ደንበኛቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 2/2009 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኮሎኔል ደመቀ ጉዳይ የአካባቢው ሕዝብ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት እዚያው ጎንደር ከተማ ውስጥ እንዲታይ መወሰኑን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ንጉሡ ጥላሁን አመልክተዋል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ →listen