በምዕራብ አማራ የተለያዩ አካባቢዎች እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው – VOA
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በጎንደር፣ በአዴት፣ በዳንግላና ሌሎችም ሥፍራዎች የታሠሩ ሰዎች መኖራቸውንና የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ ዋና ፀሐፊም እየተፈለጉ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ ስለሁኔታው መረጃ እንደሌላቸው የኮሚቴው ዋና ፀሐፊ አቶ ተሻገር የሚሠሩበት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፀጥታና የደኅንነት ኃላፊ አመልክተዋል፡፡
እንዲሁም ዳንግላ ላይ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ – መኢአድ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የፓርቲው የሰሜን ቀጣና ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ዐይናለም ተይዘው ዳኛ ፊትም ሳይቀርቡ፣ ክሥም ሳይመሠረትባቸው ለአሥር ቀናት መታሠራቸውን ባለቤታቸው ገልፀዋል፡፡
አዴት ላይም የፓርቲው የይልማና ዴንሣ ወረዳ ተጠሪ የሆኑት አቶ ስመኘው ገሠሠ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ተኩል ላይ ከመኖሪያ ቤታቸው በታጣቂዎች ተይዘው መታሠራቸውና ወደ ብር ሸለቆ መወሰዳቸውን የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
በተለያዩ አካባቢዎችም በርከት ያሉ የጅምላ እሥራቶች እየተከናወኑ ሲሆን እንቅስቃሴዎቹ የተሣሣቱ ወጣቶችን ለማስተማር፤ በወንጀል ተጠያቂ ስለመሆናቸው ማስረጃ ያለባቸውን ደግሞ ሕግ ፊት ለማቅረብ ነው ሲሉ የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አስረድተዋል፡፡
ሙሉውን ዘገባ ያዳምጡ → listen