የቆሎ ተማሪ በአሜሪካ – VOA


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያን ቋንቋ፣ ታሪክና ባህል ለበርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዳጊ ህፃናትንና ወጣቶችን በማስተማር ላይ ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት መካከል በሜሪላንድ የሚገኘው የደብረ ገነት መድሃኒያለም ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አንዱ ነው። በዚሁ ቤተክርስቲያን በምክትል አስተዳዳሪነትና በቅዳሴ በማገልገል ላይ የሚገኙት መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ገብረወልድ አገዝ ወደ ቤተክርስቲያኒቱ የሚመጡትን በርካታ አዳጊ ሕፃናትን የሃይማኖት ትምህርት ጨምሮ የኢትዮጵያን ታሪክና ቋንቋን በማስተማር ላይ ይገኛሉ።

በአሁኑ ስዓት ትምህርቱን በመከታተል ላይ የሚገኙት አዳጊ ሕፃናቶች እድሜያቸው ከ6-16 አመት ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 3ቱ ከኢትዮጵያ የድቁና ማዕረግን እስከመቀበል ደርሰዋል። መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ገብረወልድ አገዝንና የሚያስተምሩዋቸው አዳጊ ሕጻናት ከመስታወት አራጋው ጋር ቆይታን አድርገዋል። ያዳምጡ → listen