ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ እንዲሁም አባቱ አቶ ኢሳያስ ገ/ወልድ እንዲሁም የቤተሰቡ ጠበቃ እና የህግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅን ውሳኔ እንደማይቀበለቱ ገለፁ።
ዩኒቨርሲቲው ውሳኔውን እንዲቀለብስ እና ተማሪ ቢንያምን ከ4 ዓመት በላይ ወደለፋበት የትምህርት ገበታው እንዲመልሰው ጠይቀዋል።
ይህንን የጠየቁት " ሸገር ኢንፎ " በሚሰኝ የዩትዩብ ገፅ ላይ በቀረቡበት ወቅት ነው።
የተማሪ ወላጅ አባት አቶ ኢሳያስ " ውሳኔው ተቀባይነት አለው ብዬ አላስብም ፤ በውሳኔውን አዝኛለሁ አልቀበለውም፤ ውሳኔውን ተመልሰው እንዲያጤኑት " ሲሉ ጠይቀዋል።
" በሌላ ዓለም እንክብካቤ እየተደረገ እውቀት ያለው ጭንቅላት ያለውን ኡፍኡፍ እያሉ ነው የሚይዙት እዚህ ሳየው ተቃራኒ ሆኖብኛል " ሲሉ ገልፀዋል።
አቶ ኢሳያስ ልጃቸው ወደፊት ትልቅ ደረጃ ደርሶ የህዝቡ አገልጋይ ሆኖ እንደሚመጣ ምንም ጥርጥር እንደሌላቸው ተናግረዋል።
ተማሪ ቢንያም በበኩሉ ፤ ውሳኔው ከዚህ በፊት ከነበረው ያልተለየ መሆኑን ገልጾ " በእነሱ ምክንያት ሀገሪቱ እየከሰረች ነው " ሲል ገልጿል።
" እኔ ፕሮሰሱን ጠብቄ ነው የገባሁት እኔ ባላጠፋሁት ምን አይነት ኃላፊነት እንደወሰዱ አልገባኝም ፤ እኔን ማብቃት ነው የሚገባቸው እንጂ ቴክኒካል ጉዳዮችን ጠቅሰው መናገራቸው ሲሉት የነበሩትን ነው የደገሙት ለእኔ የተለየ ውሳኔ አይደለም፤ የተለየ ውሳኔም አልጠበኩም " ብሏል።
ተማሪ ቢንያም ዩኒቨርሲቲው የለፋበትን ትምህርት ሊያስጫርሰው እንደሚገባ ገልጾ በሌላ ዓለም ላይ ያሉ ተሞክሮዎችን መውሰድ ይቻላል ብሏል።
ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ፤ ዩኒቨርሲቲው ውሳኔውን ድጋሚ እንዲያጤነው ካልሆነ ወደ ክስ እንደሚገባ ተናግረዋል።
- Category
- Ethiopian News