የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል ይወጣሉ ብለው እንደማያምኑ የአማጺው ሕወሃት ሥራ አስፈጻሚ አባል ጌታቸው ረዳ ዛሬ ለአልጀዚራ በሰጡት ቃል ተናግረዋል፡፡ ባሁኑ ሰዓት በፌደራል መንግሥቱ እና በአማጺው ሕወሃት መካከል አንዳችም የግንኙነት መስመር እንደሌለ ጌታቸው ገልጠዋል፡፡ ነጻ ትግራይን የመመስረት ዕቅድ ስለመኖሩ ተጠይቀውም፣ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ነጻ ትግራይን አሳማኝ አማራጭ እንዲሆን እያደረገው ነው ብለዋል፡፡
- Category
- Ethiopian News