Loading...

ደቡብ አፍሪካ አሜሪካ በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ ጠየቀች።

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

ANC SG Ace Magashule calls for resolve as tensions simmer between Ethiopia and Egypt

በህዳሴው ግድብ ጉዳይ አሜሪካ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ ደቡብ አፍሪካ ጠየቀች።

 
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከት አሜሪካ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነት ሥፍራን የያዘችው ደቡብ አፍሪካ ጠይቃለች።
-
የደቡብ አፍሪካ መንግስትን በመወከል መግለጫ የሰጡት የገጂው ANC (African National Congress) ፓርቲ ዋና ፀሀፊ ኤስ ማጋሹሌ የአፍሪካ ጉዳዮችን አፍሪካዊያን ለመፍታት አቅሙ ስላላቸው የውጭ ጣልቃ ገብነትን አንፈቅድም ብለዋል።
-
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ከትላንት በስቲያ የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ ያደረጉት ኃላፊነት የጎደለው ንግግር ተቀባይነት የሌለውና ከአፍሪካ ህብረት አቋም ጋር የሚጋጭ መሆኑን ገልጸዋል።
-
ከደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቴሌቪዥን SABC ጋር ቆይታ ያደረጉት ዋና ፀሀፊው የህዳሴው ግድብ ጉዳይ የእኛ የአፍሪካዊያን ጉዳይ በመሆኑ የየትኛውንም የውጭ ሃይል ጣልቃ ገብነት አንፈቅድም ብለዋል።
-
የትራምፕ አስተያየት የአፍሪካን ብሎም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያላከበረ መሆኑን ያነሱት ዋና ፀሃፊው ፀብ አጫሪ ግለሰቦች በአፍሪካ ቦታ የላቸውምም ብለዋል።
የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር እና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሴርል ራማፎዛ ጉዳዩን ከኢትዮጵያ እና ግብጽ ጋር በመነጋገር ለመፍታት መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን SABC ዘግቧል።
 

ANC SG Ace Magashule calls for resolve as tensions simmer between Ethiopia and Egypt

Tension is simmering between Ethiopia and Egypt as the African Union continues to seek a solution to problems caused by the building of the Great Renaissance Dam on the river Nile. AU Chairperson President Cyril Ramaphosa has been requested by Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed to intervene in the standoff between Ethiopia and Egypt about the building of the dam.
Yesterday US President, Donald Trump dropped a bombshell saying Egypt might bomb the dam if no solution is reached. Former Prime Minister of Ethiopia Hailemariam Dessalen has spoken out against President Donald Trump's comments, referring to it as reckless.
The former Prime Minister tweeted that Ethiopians will never be threatened by his irresponsible statements, adding that history will teach everyone.

Category
Ethiopian News

Post your comment