We Are Witnessing The !NVASION Of Ethiopia by "Foreign Forces"! || Wake Up Africa
They told us they would do this and now it looks like the Divided States, Isr@el & Egypt are behind the "civil unrest."
በአፍሪካ ምድር ድሮም ክብሯን በወራሪ ሳታስደፍር የኖረችው ኢትዮጵያ ዛሬም ነጮቹን ዳግም ድል እንደምታደርግ አምናለሁ ስትል አፍሪካዊቷ የቴሌቪዥን ሾው አዘጋጅ ዶክተር ሙምቢ ሴራኪ ገለፀች።
ዶክተር ሙምቢ ሴራኪ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ለቴሌቪዥን ተከታታዮቿ ባዘጋጀችው መሰናዶ ኢትዮጵያ ለብቻዋ ከምዕራባዊያን ሀይሎች ጋር ጦርነት ላይ እንደሆነች ገልጻ በስተመጨረሻ ድል የምታደርገው ኢትዮጵያ እንደሆነች እንደምታምንም ተናግራለች።
ሊቢያ ላይ ወረራ የፈጸመው “ቲም ኦባማ” ጆ ባይደንን ተከትሎ ነጩ ቤት ገብቷል ያለችው ዶክተር ሙምቢ ይሄ ትግል በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተ ዘመቻ ሳይሆን መላው አፍሪካን ኢላማ ያደረገ ነው በማለት ተናግራለች። “የአፍሪካ እንቅልፋም ፕሬዝደንቶች” መች እንደሚነቁ አላውቅም፤ ነገር ግን ኢትዮጵያዊያን ለብቻቸው ሆነው ቀኝ ገዢዎችን እየረቱ ነው ስትል የገለጸችው ዶክተር ሙምቢ ለአፍሪካዊያን የማትተኛው ግብጽ ከዚህ ሁሉ ሁከት ጀርባ እጇ እንዳለበት እንደምታምን ተናግራለች።
ግብጽ እነአሜሪካን ሳይቀር ከጎኗ ይዛ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲ ማሸነፍ ሲሳናት አሸባሪዎችን አስታጥቃ ቀጠናውን እያተራመሰች ትገኛለች ያለችው ዶክተር ሙምቢ ይሄም ሆኖ ግን አይሳካላቸውም ኢትዮጵያ ዳግም ድል እንደምታደርግ አምናለሁ ብላለች።
ዶክተር ሙምቢ በመጨረሻ ለአፍሪካዊያን ባስተላለፈችው መልዕክት እንደCNN ያሉ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚያሰራጩትን ሀሰተኛ ዘገባ በማጋለጥና ትክክለኛ መረጃ በማጋራት ኢትዮጵያን እናግዛት ስትል ጥሪ አቅርባለች።
- Category
- Ethiopian News