President Biden’s designate Ambassador to United Nations Linda Thomas-Greenfield has the following to say about Ethiopia “...Ethiopia is in the middle of a war against its own people..It is important the United Nation Security Council take this situation on”
በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ ዕጩ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ሹመታቸውን ለማጽደቅ ለተሰየመው የላይኛው ምክር ቤት ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵ መንግሥት ከገዛ ሕዝቡ ጋር ጦርነት ገጥሟል- ብለዋል ግሪንፊልድ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለዚህ ሁኔታ ምን ምላሽ መስጠት እንዳለበት እንዲያሰላስልም መክረዋል፡፡ በክልሉ የሰብዓዊ ሁኔታው እንዳሽቆለቀለ የገለጹት አምባሳደሯ፣ ተመድ ከመንግሥት ጋር ግልጽ ንግግር ማድረግ እንደሚያስፈልገው አውስተዋል፡፡
- Category
- Ethiopian News