መንግስት ለፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲከፋፈል በዚህ አመት ከመደበው 98 ሚሊዮን ብር ውስጥ፤ የተወሰነው መጠን በሚቀጥለው ሳምንት ለፖለቲካ ፓርቲዎች መከፋፈል ሊጀመር ነው። ለፓርቲዎች የሚሰጠው ገንዘብ ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩልነት እንዲከፋፈል በቀመር አማካኝነት የተደለደለ ነው ተብሏል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተዘጋጀው የክፍፍል ቀመር መሰረት መንግስት ለፓርቲዎች ከሚመድበው ገንዘብ ውስጥ 25 በመቶ ያህሉ፤ በቦርዱ ዕውቅና ተሰጥቷቸው ለሚንቀሳቀሱ ለሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩልነት ይከፋፈላል። የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ቅዳሜ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ እንደተናገሩት፤ “የገንዘብ ድጋፍ ከምርጫ ጋር ብቻ የተገናኘ አይደለም”።
“መንግስት፤ ፓርቲዎች የህዝብ ፍላጎት aggregate እያደረጉ፣ ወደ አማራጭና ወደ ፖሊሲ ለሚቀይሩ ፓርቲዎች ሁልጊዜም ድጋፍ የማድረግ ግዴታ አለበት” ብለዋል ሰብሳቢዋ። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎቻችን ለመከታተል፦
ድረ ገጽ ፦ http://ethiopiainsider.com
ፌስቡክ ፦ https://www.facebook.com/ethiopiainsider
ትዊተር ፦ https://twitter.com/ethiopiainsider
#ምርጫ #ምርጫ_ቦርድ #ብርቱካን_ሚደቅሳ #ኢትዮጵያ #Ethiopia
- Category
- Ethiopian News