Loading...

ከሕወሓት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ አስር ሕፃናትና ወጣቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በደሴ ሆስፒታል እየታከሙ ነው

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

"ቤታችን ቁጭ ብለን እያለ አሸባሪው ቡድን በከባድ መሳሪያ መትቶናል፤ አከራዬ ሲሞት እኔና ባለቤቴ ጉዳት ደርሶብናል።" በከባድ መሳሪያ ጉዳት የደረሰባቸው የመሆኒ ከተማ ነዋሪዎች

በምዕራብ ትግራይ አካባቢ በነበረው ጦርነት አስር ቤተ-ዘመዶች በከባድ መሳሪያ ጥቃት ቆስለው በደሴ ሆስፒታል በህክምና ላይ መሆናቸው ተነገረ። የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪየጅ አቶ ሰኢድ ዩሱፍ እንደተናገሩት ቤተ-ዘመድ የሆኑን እና ከ 7 እስከ 14 እድሜ የሆናቸው ህፃናትና ታዳጊዎች በእጅጉ ተጎድተው በህክምና ላይ ይገኛሉ ብለዋል። የወንድምና የእህት ልጆች ከሆኑት ከእነዚህ ተጎጅዎች መካከል ሁለቱ ወላጆቻቸውን በደረሰዉ ጥቃት አጥተዋል ተብሎአል።
በሆስፒታሉ ሕክምና እየተደረገላቸዉ ያሉት “አስሩ ሕፃናትና ወጣቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ከእነዚህ መካከል 4ቱ እግራቸው ተቆርጧል፣ ሌሎች ደግሞ ከባድ የአጥንት ስብራት የደረሰባቸዉ ናቸዉ ሲሉ አቶ ሰኢድ ዩሱፍ አክለዋል። የአማራ ክልል ቴሌቪዝን በዛሬዉ የቀትር የዜና እወጃዉ እንደዘገበው ጥቃቱ በትግራይ ክልል መኾኒ በተባለች ከተማ ህዳር 11/2013 ዓ.ም በህወሓት ታጣቂዎች ባደረሱት የከባድ መሳሪያ ተኩስ መሆኑን ዘግቧል፡፡
Category
Ethiopian News

Post your comment