"ከዚህ በሗላ የጦር ሰራዊትን ከሗላው አሰልፎ ለሚመጣ የተደራጀ ዘራፊና አውዳሚ ምህረት የለንም" - ብ/ጄ ተፈራ ማሞ
ህወሃት የተደራጀ ዘረፋ ለማድረግ ነው እቅዱ። ሌላ ወታደራዊ ግብ የለውም። በየትም አለም ጦርነት የሚደረገው በሰለጠኑ ሃይሎች መካከል ነው።
ጁንታው ግን ወይ የጅምላ ፍጅት እንዲካሄድ፣ ከቀናውም በጅምላ ለመዝረፍ ህዝብን በተሳሳተ መንገድ በማንሳሳት ከፊት አሰልፎ ነው የሚጎርፈው። ከዚህ በሗላ ግን የጦር ሰራዊትን ሗላው አሰልፎ ለሚመጣ የተደራጀ ዘራፊ ምህረት የለንም።
ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ - ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተናገሩት
- Category
- Ethiopian News