#Ethiopia #Shewa #Minjar_Shenkora
የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ቦሰት ለቪኦኤ ፦
" አውራ ጎዳና የምትባለው የአሞራ ቤት ቀበሌ መንደር ነች። ሰው ከፊል አርሶ አደር የሆነ በንግድም ጭምር የሚተዳደር ነው።
በዕለቱ ጥዋት አካባቢ አንዳንድ ምልክቶች ነበሩ 4 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ ከዛ በኃላ ወደ ቀን 7 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ መሳሪያ የጫኑ በልዩ ልዩ በአይሱዙ ፣ በመሳሰሉ መኪናዎች ጭነው የመጡ ሰዎች አልፍ ሲልም የመንግስት ተሽከርካሪ ጭምር የተጠቀሙ ሰዎች ናቸው የመጡት።
የቡድን መሳሪያም አጥምደው ነው የመጡት መጀመሪያ ላይ በአውራ ጎዳና ከተማ ውስጥ አለፉ ከዛ መጨረሻ ላይ ዳር ላይ ሲደርሱ የፌዴራል ፖሊስ ምንድነው ሲላቸው መጀመሪያ እሱን ገደሉ ከዛ ተመልሰው ወደ ማህበረስቡ ገቡና ወደ 8 ሰዓት አካባቢ በጣም የጦፈ ጦርነት ውስጥ ነበር የተገባው።
አመሻሽ 12 ሰዓት አካባቢ ነው ተኩስ እየቆመ የመጣው ፤ ድንገቴ ስለሆነ ሰውም ባላሰበበት ሰዓት ስለሆነ ከባድ ችግር ነበር የነበረው።
እንደምንም ብሎ የአካባቢው ማህበረሰብ እራሱን ለማዳን ጥረት አድርጎ ሴቶች እና ህፃናትን አሽሽቶ ሌላውን አካል እዛው ባለበት ለማድረግ ተሞክሯል።
የአካል ጉዳት ፣ የሞት ፣ የንብረት ጉዳት ና መፈናቀል ጭምር ነው የተፈጠረው። "
- Category
- Ethiopian News