#ChenaMassacre #Ethiopia #TPLFisaTerroristGroup
ጭና ቀበሌ ዳግማዊ ማይካድራ ሆናለች፤ በሕወሓት የተገደሉ ንፁሃን 200 ደረሰ; በጭና ሚካኤል አቅራቢያ 59 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በጅምላ ተቀብረዋል።
ከአንድ ቤተሰብ 5 እና 6 ሰዎች የሞቱ አሉ" የጭና ነዋሪዶች
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ወረዳ "ጭና" ተብሎ በሚጠራ ቦታ የህወሓት ታጣቂዎች ከአንድ መቶ በላይ ንፁሃንን መግደላቸውን ነዋሪዎች አሳውቀዋል።
ግድያው የተፈጸመው አካባቢው በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር በቆዩባቸው ቀናት ውስጥ ሲሆን ሽማግሌዎች፣ ሴቶችና ህጻናት በተፈጸመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።
አንድ የጭና አጎራባች ቀበሌ አብጥራ፣ ነዋሪ የሆኑ አስማረ ታፈረ የተባሉ ግለሰብ ለቢቢሲ በሱጡህ ቃል ፥ ነሐሴ 12 ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ በአካባቢው የህወሓት ታጣቂዎች በመግባት ተኩስ መክፈታቸውንና ውጊያ መካሄዱን ጠቁመዋል።
ጦርነቱ እስከ ነሐሴ 29 ድረስ መካሄዱን የገለፁ ሲሆን፥ እስካሁን ድረስ ተገድለው የተገኙ 119 ሰዎች በጦርነቱ ያልተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው ብለዋል።
"ይህ ቁጥር መሞታቸው ታውቆ ለቅሶ እየተለቀሰ ያለ ነው" በማለት ይህ ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል።
እንደነዋሪው ገለፃ፥ ከአንድ ቤተሰብ 5 እና 6 ሰዎች ሞተዋል።
ዛሬ ደግሞ ሌሎች የአይን እማኝ ነን ያሉ ነዋሪዎች በጭና ተክለሃይማኖት ቀበሌ የተገደሉ ንፁሃ ከ200 በላይ መሆናቸውን አመልክተዋል። 193 የሚሆኑት በጭና ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን መቀበራቸውን አመልክተዋል።
ከ20 በላይ የሚሆኑት በዲያ ጊዮርጊስ መቀበራቸውን አሳውቀዋል።
አሁንም ተጨማሪ አስከሬን እየተገኘ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን የደረሱበት ያልታወቀ እንዳሉም ነው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
- Category
- Ethiopian News