Loading...

‹‹ኦሮ-ማራ የፖለቲካ አቅጣጫውን ከኢሳት ስለሚቀበል ራሳችንን ከስምምነቱ አግልለናል›› ፕ/ር መረራ ጉዲና

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

Ethiopia Today : ‹‹ኦሮ-ማራ የፖለቲካ አቅጣጫውን ከኢሳት ስለሚቀበል ራሳችንን ከስምምነቱ አግልለናል›› ፕ/ር መረራ ጉዲና

በትናንትናው ቀን መስከረም 13፡2013 ዓ.ም በኦሮሚያና በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በሚያራምዱት የፖለቲካ አቋሞች ላይ የስምምነት ፊርማ መፈራረማቸውን ተከትሎ፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የፊርማው አካል እንደነበር በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የቀረበው ዘገባ የሐሰት መሆኑን የድርጅቱ ሊቀመንበር ፕ/ር መረራ ጉዲና ለ’ኢትዮጵያ-ቱዴይ’ አሳውቀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በኦሮሚያና አማራ ክልል በሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሓከል ሲደረጉ በነበሩት ውይይቶች ላይ ድርጅታቸው ተሳትፎ እንደነበረው የሚናገሩት ፕ/ር መረራ፣ ከአርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ እና በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ECA) አዳራሽ በአገራዊ መግባባት ዉይይት ላይ የጥናት ወረቀት ማቅረባቸውን ተከትሎ ተቀናቃኞቻቸው በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) እየተመሩ አላፈላጊ አሉታዊ ነገሮችን በማካሄዳቸውና ሕዝባቸዋም ከዚህ ስምምነት የሚጠቀመው ነገር ባለመኖሩ ድርጅታቸው ከዚህ ስምምነት ራሱን ማግለሉን ለአስተባባሪዎቹ ቀድመው ማሳወቃቸውን ተናግረዋል፡፡

© ethiopia-today.com

Category
Ethiopian News

Post your comment