[ከኢሳት አፈትልኮ የወጣው የድምፅ ማስረጃ] የዶ/ር አብይ ድብቅ ሚስጥር የያዘው የድምፅ ማስረጃ አፈትልኮ ወጣ
አንድ ከባድ ሚስጥራዊ መረጃ #በኢሳት (ESAT) ሪከርድ ክፍል ውስጥ ለሰባት (7) አመታት ያህል ተቆልፎበት ቆይቷል። በእርግጥ መረጃው በወጣበት ሰሞን በጣም አነጋጋሪ ሆኖ ነበር። የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በተቃዋሚዎች እና ዜጎች ላይ የሚያካሄደውን የስለላ ተግባር፣ የተለያዩ ሚዲያዎችን #ጃም ለማድረግ፣ እንዲሁም የስልክና ኢንተርኔት መረጃ ልውውጦችን ለመጥለፍ የሚጠቀማቸውን ዘዴዎችና ይህን ተግባር በበላይነት ስለሚመራው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (#INSA) ከዚያ በፊት ተሰምተው የማያውቁ መረጃዎች ወጥተዋል። ነገር ግን በለውጡ ማግስት በተለይ ደግሞ የለውጡ ወረት ካለቀበት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ለሰባት አመታት ያህል በኢሳት ሪከርድ ክፍል ተቀምጦ የከረመው መረጃ እንደ አዲስ ማነጋገሩን ቀጠለ። ይህም የሆነበት መሠረታዊ ምክንያት ከላይ በተጠቀሰው ሚስጥራዊ መረጃ ላይ ስማቸው በተደጋጋሚ የተነሳው በወቅቱ በኮሎኔል ማዕረግ በINSA በዳይሬክተርነት ደረጃ ቁልፍ ሰው የነበሩት ግለሰብ የለውጡና የሀገሪቱ መሪ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመሆናቸው ነው። በዚህ ረገድ በAbebe Gellaw እና በErmias Legesse Wakjira መካከል የነበረው ክርክር በብዙዎች ዘንድ ግራ መጋባት እና ጉዳዩን ለማወቅ ከፍተኛ ጉጉት የጫረ ሆኖ ሰንብቷል። በኢትዮጵያ አዲስ አመት ዋዜማ ላይ የቀድሞ የኢሳት ባልደረባ የሆነው ኤርሚያስ ለገሰ "ጋዜጠኛ አበበ ገላው ስለ ዶ/ር አብይ ብዙ ሚስጥር የያዘውን የድምፅ ቅጂ እንዲያወጣና ህዝብ እውነታውን እንዲያውቅ" በማለት ጥሪ አቅርቧል። በአንፃሩ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ደግሞ የተጠቀሰው መረጃ በአቶ ኤርሚያስ ለገሰ እጅ እንደሚገኝና በራሱ ሊያወጣው ይችላል በማለት ምላሽ ሰጥቷል። በሁለቱ መካከል ያለው ክርክር በጥሞና ካጤንኩ በኋላአቶ ኤርሚያስ ለገሰ በእጁ ላይ ያለውን መረጃ ሌላ ሰው እንዲያወጣው ከመጠየቅ ይልቅ እሱ በራሱ ማውጣት አለበት የሚል አስተያየት ሰጥቼ ነበር። በተለይ ደግሞ ለአበበ ገላው በይፋ ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ኢሳትም ሆነ አበበ ገላው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ በእጁ ላይ የሚገኘውን መረጃ እንዲያወጣ ፍቅድና ይሁኝታ የሰጡት ቢሆንም ባለፉት አስር ቀናት ውስጥ መረጃውን አላወጣም። በዚህ ግራ መጋባት ውስጥ እያለን ይህ አነጋጋሪና አወዛጋቢ የሆነው ሚስጥራዊ መረጃ አፈትልኮ ከእጃችን ገብቷል። #EthioWikiLeaks የደረሰውን መረጃ እንደወረደ እንሆ በረከት ብሏችኋል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በራሱ ሰምቶና አይቶ መፍረድ፣ መውደድ አሊያም መጥላት ይችላል። ይህ መረጃ በመውጣቱ የሚጎዳው ውሸትና ውሸታሞች ብቻ ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ "በእጃችን ላይ ከባድ ሚስጥር አለ" እያሉ ዘወትር ጠዋት ማታ ውሸትና ተንኮል ከሚግቱት አሻጥረኞች ይልቅ ሚስጥራዊውን መረጃ በይፋ አውጥተው ቢነግሩት አስቦና አገናዝቦ ለእሱ የሚበጀውን በራሱ መወሰን ይችላል በሚል ፅኑ እምነት ለዘጠኝ አመታት ያህል ተደብቆ፣ ላለፉት ሁለት አመታት ደግሞ ሲያጨቃጭቅ የነበረውን መረጃ አቅርበንላችኋል። የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ማዳመጥ ይቻላል።
- Category
- Ethiopian News