Blog Archives

የጥቁር አዝሙድ ዘይት 32 የጤና ጥቅሞች

የጥቁር አዝሙድ 32 የጤና ጥቅሞች 1ኛ. ለእርጋታ አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መውሰድ ቀኑን ሙሉ መረጋጋትና ንቃት ያጎናጽፋል፡፡ እንዲሁም ከራት በኋላ ወደ መኝታ ከማምራት በፊት አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት መውሰድ ለሊቱን ሙሉ የተረጋጋና ደስ የሚያሰኝ እንቅልፍ ያስገኛል፡፡ አንድ ትልቅ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሲኒ ቡና ውስጥ ጨምሮ መጠጣት፡፡ የአእምሮ ጭንቀትን አስወግዶ መረጋጋትን ያስገኛል፡፡ 2ኛ. ለሳልና ለአስም በዘይቱ ደረትንና ጀርባን ማሸት በቀን ሦስት የሾርባ ማንኪያ መጠጣት፣ ሁለት ማንኪያ በሙቅ ውኃ ውስጥ ጨምሮ እንፋሎቱን መሳብ ይረዳል፡፡ 3ኛ. የመጫጫንና ስንፍናን ለማስወገድ አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት በአንድ ብርጭቆ ብርቱካን ጭማቂ ውስጥ ጨምሮ ጧት ጧት ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ ልዩነቱን ያገኙታል፡፡ 4ኛ. የማስታወስ ችሎታንና ፈጣን የግንዛቤ አቅምን ለማጎልበት አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት፣ 100 ሚሊ ሊትር የፈላ ናእናእ (Nena) ተክል ጋር ተቀላቅሎ ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ፡፡ 5ኛ. ለኩላሊት ጠጠር (የስኳር ሕመም ያለባቸው ማርን መተው ነው) ሩብ ኪሎ ጥሬ ጥቁር አዝሙድ፣ ሩብ ኪሎ ንጹሕ ማር ማዘጋጀት፡፡ ጥቁር አዝሙድን በሚገባ መፍጨትና ከማር ጋር ቀይጦ በሚገባ ማዋሀድ፡፡ ከዚያም ሁለት ማንኪያ ከቅይጡ ቀንሶ በአንድ ብርጭቆ የሞቀ ውኃ ውስጥ ጨምሮ በጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሻይ ማንኪያ በማከል በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡ 6ኛ. ለብሩሕ ገጽና ለውበት አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ማንኪያ የወይራ ዘይት ጋር አዋሕዶ ፊትን መቀባት አንድ ሰዓት ቆይቶ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News