Blog Archives

በኤርትራ የሚገኘው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) ጸረ መንግስት የኃይል ጥቃቶችን በጊዜያዊነት ለማቆም ውሳኔ ላይ ደረሰ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) ጸረ መንግስት የኃይል ጥቃቶችን በጊዜያዊነት ለማቆም ውሳኔ ላይ ደረሰ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ነገድ ላይ ያነጣጠሩ የቀጥታና የእጅ አዙር አሰቃቂ ጅምላ ጸረ አማራ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ዘመቻዎች በአሻጥርና በሴራ በብሄራዊ ደረጃ መታወጃቸውን ተከትሎ የትጥቅ ትግል ለማካሄድ የተገደደውና ጸኑ የህልውና ትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ያለው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) በጦር መሳሪያ የሚካሄዱ ጥቃቶችን ሁሉ በጊዜያዊነት ለማቆም ወስኗል። በዘር መፈረጅና መገፋት ብሶትና ምሬት ከአንገበገበው ከመላ አማራ ህዝብ ጎን በመሰለፍ በትጥቅና ያለትጥቅ በይፋና በህቡዕ እስከ ህይወት መሰዋዕትነት በመክፈልና አማራ ከነፍስና ስጋው ከተዋሃዱ ብሄራዊ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት እኩል በአማራ ብሄርተኝነት ስሜት ወደ አንድ በመምጣት በእራሱና በሀገሩ ህልውና ላይ የተቃጡ አደገኛ የጥፋት ዘመቻዎችን በጠንካራ ክንዱ እንዲቀለብስ በማድረግ ከፍተኛ ሚና የተጫወተው አዴኃን በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ሀገራችን እየተካሄደ ያለውን አንጻራዊ የለውጥ ጅምር ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለብሄራዊ መረጋጋትና ምቹ የፖለቲካ ምህዳር ለመፍጠር ሲባል የተደረገውን አገራዊ ጥሪ በመቀበል በጦር መሳሪያ ኃይል የሚካሄዱ ማናቸውንም ጸረ መንግስት ጥቃቶችን ከመሰንዘር በጊዜያዊነት ማቆሙን እየገለጸ በህዝባዊና ብሄራዊ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር የልዑካን ቡድኑን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክም ውሳኔ ላይ ደርሷል። ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ትጥቅ ትግል እንዲያካሄድ ያስገደዱት የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ስለተመለሱ ሳይሆን፣ አማራው አስደናቂ በሚባል ደረጃ እራሱንና ሌሎች በዘር ማጥፋት ቀለበት ውስጥ የገቡ ወገኖቹን ታግሎና አታግሎ ለማዳን ሲል በአማራ ብሄርተኝነት የተነሳሳበትና በንቁ ስሜት የተደራጀበት ወቅት በመምጣቱ ብሎም በሀገራችን በሰላም
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News