Blog Archives

የአቃቂ ወንዝ ሞልቶ በመገንፈሉ በሰው ላይ አደጋ ጋርጦ እንደነበር ተሰማ።

አዲስ አበባ ዛሬ ማለዳ ላይ የአቃቂ ወንዝ ሞልቶ የትራንስፖርት መስተጓጎል እና በሰው ላይ አደጋ ጋርጦ እንደነበር የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ዛሬ ነሐሴ 16፣20110 ከማለዳው 12፡15 ላይ የአቃቂ ወንዝ ሞልቶ በመገንፈሉ ሀያ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በውሃ ሙላት ተይዞ አደጋ ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ማትረፍ መቻሉን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡ በውሃ ሙላቱ ህይወታቸውን ለማትርፍ ተሳፋሪዎች በመኪናው አናት ላይ ለመቆየት ተገደዋል፡፡ የተሳፋሪዎቹን ህይወት ለማትረፍ የአየር ኃይል ሄሊኮፍተርን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን ባለሞያዎችና ዋናተኞች ልዩ ልዩ ማሽነሪዎችን በመታገዝ ያደረጉት ርብርብ እንደተሳካቸው የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ  አስታውቀዋል፡፡ ሰዎቹን ለተጨማሪ ምርመራና ህክምና ወደ አቃቂ ጤና ጣቢያ መላካቸውንም አመልክተዋል፡፡ ኢቢሲ  
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News