Blog Archives

የተዘነጉት የዜግነት እሴቶችና የኢትዮጵያ ቀጣይ ጉዞ ( አብርሃም ገብሬ )

ኢትዮጵያ ውስጥ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ማሳረጊያው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት ከሆነ፣ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመዝለቅ በየትኛው መንገድ ነው መጓዝ የሚያስፈልገው? የዲሞክራሲ መዳረሻ መንገዱ የሚመረጥበት መስፈርትስ ምን መሆን አለበት? ከሁኔታዎች ጋር እራሱን እያደሰ የሚሄድ፤ ቀጣይነት ያለው ዲሞክራሲያዊ ስርዓትስ እንዴት መመስረት ይቻላል? የሚሉትን ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ ከተቻለ፣ ለዛሬዋ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን፣ ለመጪው ትውልድ የሚሆኑ መልካም እሴቶችን በጽኑ መሰረት ላይ አኑሮ ማለፍ ይቻላል፡፡ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመተግበር ሰፊ ልምድ ያዳበሩ አገራት፣ ከነገድ ጋር የተያያዙ ማንነቶችንና ሌሎችንም ፈርጀ-ብዙ ልዩነቶቻቸውን አስታርቀው የሚጓዙበትን መላ ይዘይዳሉ፡፡ መልከ-ብዙ ልዩነቶቻቸውን ለማቻቻል ካስቻሉዋቸው ዘዴዎች መካከል አንዱ የ“ዜግነት” (Citizenship) ስርዓተ ማህበር ነው፡፡ በተለይም የግለሰብንና የነገዳዊ ስብስቦች መብትን ለማረቅ የዜግነት ዕሴቶች አስፈላጊነት አጠያያቂ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም የነገድና የግለሰብ መብት አሰናኝቶ ወደፊት ለመጓዝ የሚያስችል ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ዕውን ማድረግ በእስካሁኑ ጉዞ አልተቻለም፡፡ ለነገዳዊ ስብስቦች እውነተኛ የሆነ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቶቻቸውን በማረጋገጥ፣ የሃገሪቱን ዋነኛ አስተሳሳሪ ማንነትን ግን በዜግነት መሰረት ላይ በማቆም የሁሉም መብት የሚከበርበት ስርዓት ለመዘርጋት አልተሞከረም፡፡ ስለዚህ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ አብቦ ፍሬ እንዲያፈራ፣ የዜግነት ዕሴቶችን ማዕከል ያደረገ ስርዓት ማቆም ያስፈልጋል፡፡ ዜግነትን ማዕከል የሚያደርግ ስርዓትን ተመራጭ የሚያደርገው፣ መልከ-ብዙ ልዩነቶችን የማስተናገድ አቅም ስላለው ነው፡፡ ነፃነት ዜግነት መብቶች ግዴታዎች ዜግነት፤ ግለሰቦች አገሬ ብለው ከሚጠሯት አገር ጋር ህጋዊ ትስስር የሚፈጥሩበትና ለአገራቸው ወገንተኝነት የሚያሳዩበት ስርዓት ነው ይላሉ – የዘርፉ ምሁራን፡፡ የትስስሩን ፍጥጥም ደግሞ በህግ ውል የሚቋጭ ነው፡፡ ይህ ህግ፤
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News