የጂቡቲ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዕቃዎች በዘመናዊ መሣሪያ በመፈተሽ በአንድ ኮንቴይነር ዕቃ፣ ከአሥር እስከ 35 ዶላር ለማስከፈል አዲስ ዕቅድ አወጣ፡፡
የጂቡቲ ወደብ አስተዳደር አዲሱን ክፍያ እ.ኤ.አ. ከጥር 15 ቀን 2016 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ፣ ለኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ማሳወቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ …
የጂቡቲ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዕቃዎች በዘመናዊ መሣሪያ በመፈተሽ በአንድ ኮንቴይነር ዕቃ፣ ከአሥር እስከ 35 ዶላር ለማስከፈል አዲስ ዕቅድ አወጣ፡፡
የጂቡቲ ወደብ አስተዳደር አዲሱን ክፍያ እ.ኤ.አ. ከጥር 15 ቀን 2016 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ፣ ለኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ማሳወቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ …
በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እየተፈተነ የሚገኘው የሲሚንቶ ኢንዱስትሪ የገበያ መቀዛቀዝ አሳየ፡፡ አገር ውስጥ የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ዓመታዊ የማምረት አቅማቸው 13 ሚሊዮን ኩንታል ቢሆንም፣ ሽያጩ ግን ከሰባት ሚሊዮን ኩንታል ያልበለጠ መሆኑ ታውቋል፡፡
በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና ከቀትር በኋላ 11፡00 ሰዓት እስከ ምሽት 4፡00 …
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅና የግዢና ንብረት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በአሥር ሚሊዮን ብር ሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታወቀ፡፡
ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ኤፍሬም ደሳለኝና የግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ንጉሤ ታደሰ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ ኅዳር 21 …
በሽብር ድርጊት ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመሥርቶባቸው ማረሚያ ቤት በሚገኙት በእነ ዘመኑ ካሴ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት በተቆጠሩት የግንቦት ሰባት አመራር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣
በመከላከያ ምስክርነት እንዳይቀርቡ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ይግባኝ ኅዳር 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ውድቅ
…
ሰሞኑን በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች በኤቲኤም ማሽን ገንዘብ ማውጣት ባለመቻላቸው፣ በአጭር የመልዕክት ጽሑፍ ገንዘብ ማውጣታቸውን በሚገልጸው መልዕክት ከፍተኛ መደናገጥ እየተፈጠረባቸው ነው፡፡
ባንኩ በበኩሉ በጊዜያዊ ገንዘብ ዝውውር የኔትወርክ ችግር ያጋጠመ ቢሆንም፣ የገንዘብ ኪሳራ እንደማይገጥማቸው ገልጿል፡፡
በከተማዋ የተለያዩ የባንኩ ቅርንጫፎችና
…
በጣና በለስና በጊቤ አንድ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች በደረሰ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና የኤሌክትሮኒክ መቆጣጠሪያ ብልሽት፣ በመላ አገሪቱ የኃይል አቅርቦ ተስተጓጉሏል፡፡ ቅዳሜ ኅዳር 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በአገሪቱ ትልቁና 460 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ላይ በሚገኘው ጣና በለስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ …
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላንን በመቃወም፣ ኅዳር 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሠልፍ ወጡ፡፡
ተማሪዎቹ በማስተር ፕላኑ ውስጥ ማንኛውም የኦሮሚያ ቦታ መወሰድ ወይም መካተት እንደሌለበት የሚያንፀባርቁ መፈክሮችን …
ከኤልኒኖ የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች የተከሰተው ድርቅ እያሳረፈ ያለው ተፅዕኖ እየሰፋ መምጣት የተረጂዎችን ቁጥር እንዲጨምር እያደረገ ነው፡፡
ሰሞኑን በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን ለመቃኘት የተንቀሳቀሰው የጋዜጠኞች ቡድን ከተመለከታቸው አካባቢዎች መካከል፣ የምዕራብና የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ውስጥ ከወራት በፊት የነበሩት …
በተጠረጠሩበት የማታለልና ሐሰተኛ ሰነድ መጠቀም ወንጀሎች የ50 ሺሕ ብርና የ40 ሺሕ ብር ዋስትና የተፈቀደላቸው መምህር ግርማ ወንድሙን፣ ፖሊስ በነፍስ ግድያ እንደሚጠረጥራቸው በማመልከቱ አለመፈታታቸው ታወቀ፡፡
ፖሊስ መምህር ግርማ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ሳያገኙ ፈቃድ እንደተሰጣቸው በማስመሰል ሐሰተኛ ሰነድ እንደተጠቀሙ …
ኤጀንሲው ቤቱን ለባለ
…
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሐሙስ ኅዳር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሪፖርተር ጋዜጣ ዋና አዘጋጆች ዘካሪያስ ስንታየሁና አሥራት ስዩም ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ቆይታ አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ ዓይነት ቆይታ ከግል የኅትመት ሚዲያ ጋር ሲያደርጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ …
ከኢትዮጵያ መድኃኒት፣ ምግብና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣን ጥቅምት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ለብሮድካስት ባለሥልጣን በተጻፈ ደብዳቤ የአንከር ወተት የቴሌቪዥን ማስታወቂያ ኅዳር 2 ቀን 2008 ዓ.ም. እንዲታገድ መደረጉን፣ የባለሥልጣኑ ሕዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ጣፋ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
ሪፖርተር ከመድኃኒት …
በደቡብ ክልል ሸካ ዞን ይዞታቸው ለኢንቨስተር በመሰጠቱ ምክንያት ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸው ጥያቄ በማቅረባቸው ‹‹ለሕግ ተገዢ አይደሉም›› በማለትና በሽፍታነት በመፈረጅ፣ በሸኮዎች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ሸካዎችን በማስታጠቅና
የእርስ በርስ ጦርነት በማነሳሳት የተጠረጠሩ፣ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ 12 ተሿሚዎች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
የደቡብ
…
የኢትዮጵያ የመድኃኒት፣ የምግብና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 1 ቀን 2015 ባሠራጨው ሰርኩላር፣ ኮዴይን የተባለው የሕመም ማስታገሻ ላልተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡
ባለሥልጣኑ ለክልሎችም ሆነ ለፌዴራል መንግሥት የጤና ቢሮዎች በላከው ደብዳቤ እንደገለጸው፣ ኮዴይን የተባለው መድኃኒት
…
ኅዳር 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ ከጓንግዙ ቻይና ወደ አዲስ አበባ በመብረር ላይ የነበረ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 777 አውሮፕላን ውስጥ የተሳፈረ መንገደኛ፣ በስካር መንፈስ ሁከት በመፍጠሩ በመንገደኞች ርብርብ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡
የበረራ ቁጥር ኢቲ607 ከ300
…
የፕላስቲክ ቱቦዎችንና መገጣጠሚያ ማሽነሪዎችን ለማስመጣትና በአገር ውስጥ ለመገጣጠም ከኢትዮጵያውያን ጋር ባለድርሻ በመሆን ያቋቋሙትን ኩባንያ መጠቀሚያ በማድረግ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤልሲ ከፍተው ካገኙት የውጭ ምንዛሪ ውስጥ ከ62.2 ሚሊዮን ብር በላይ በውጭ ባንክ በመደበቅ የተጠረጠሩ ሁለት የውጭ ዜጐች ተከሰሱ፡፡
የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ …
አቶ ደረጀ ዳዲ በሰንዳፋ ከተማ ወተት አምራች ነው፡፡ የራሱን ብቻም ሳይሆን ከአካባቢው ገበሬዎች እየሰበሰበ አዲስ አበባ አምጥቶ ለአከፋፋዮች ያስረክባል፡፡ በቀን እስከ 800 ሊትር ወተት ያቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ በቅርቡ የዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት (IRLI) ጥናትን በመጥቀስ በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ
…
የእሳቸው ተከታይና የሚሏቸውን ነገር ሁሉ ያደርጉ የነበሩን ግለሰብ ቤት በማሸጥና ገንዘቡንም እንዲፀለይበት በማለት ወስደዋል ተብለው ተጠርጥረው የታሰሩት መምህር ግርማ ወንድሙ፣ በ50,000 ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ ላይ ፖሊስ ይግባኝ ማለቱ ታወቀ፡፡
የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ
…
‹‹መያዣ አውጥተን እያፈላለግነው ነው›› ፖሊስ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሰያን ደብር ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ፣ በአካባቢው የተመደበ ፖሊስ አርሶ አደሩን ገድሎ መሰወሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
ሟች አርሶ አደር ጌቱ ዘውገ የሚባል የ27 ዓመት ወጣት መሆኑን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣
…
መምህር ግርማ ወንድሙ፣ ጥቅምት 30 ቀን 2008 ዓ.ም. በ50 ሺሕ ብር እንዲፈቱ የተፈቀደላቸው ቢሆንም አልተፈቱም፡፡ ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር አድርጐ በመመርመር ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ ቡድን፣ ጥቅምት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ …
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሐዋሳ ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅና የደንበኞች አገልግሎት መኮንን፣ በሥልጣን ያላግባብ የመገልገል የሙስና ወንጀል ክስ ጥቅምት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ተመሠረተባቸው፡፡
የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተባቸው ሶስና ሀዲስ ገበየሁ (የደንበኞች አገልግሎት መኮንን)፣
…
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ቦርድ፣ የንግድ ምክር ቤቱን ዋና ጸሐፊ ከሥራ እንዲታገዱ ወሰነ፡፡
ዘጠኝ አባላት ያሉትና በአቶ ሰለሞን አፈወርቅ የሚመራው የንግድ ምክር ቤቱ ቦርድ፣ ዋና ጸሐፊው አቶ ጋሻው ደበበ ከኃላፊነታቸው እንዲታገዱ ውሳኔ ያሳለፈው ባለፈው ሐሙስ ጥቅምት 25 ቀን
…
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ጋር በመተባበር በዘረጋው የሆቴሎች ደረጃ ምደባ ፕሮግራም መሠረት፣ አንጋፋው ሒልተን አዲስ ሆቴል ወደ ሦስት ኮከብነት ደረጃ ዝቅ አለ፡፡ ሚኒስቴሩ ጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት 68 ሆቴሎች በደረጃ
…
–በዚህ ሳምንት በማዕከል የሚደረገው ለውጥ ይፋ ይሆናል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለክፍላተ ከተማና ለወረዳዎች 1,600 አመራሮችን ሾመ፡፡ ለተሿሚዎቹ ባለፈው ሳምንት ለሦስት ቀናት የቆየ የፖሊሲ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሙስናና በብልሹ አሠራር ገምግሞ ካሰናበታቸው አመራሮች በተጨማሪ፣ ከዲፕሎማ በታች
…
ጥቅምት 20 ለ21 አጥቢያ 2008 ዓ.ም. የልጃቸውን ጓደኛ በሽጉጥ ተኩሰው በመግደል የተጠረጠሩ ሐኪም፣ ከነመሣሪያቸው በቁጥጥር ሥር ውለው እየተመረመሩ መሆኑ ታወቀ፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 13/14 ልዩ ሥፍራው ማጂክ ካርፔት በሚባለው ትምህር ቤት አካባቢ የተገደለው ወጣት ቴዎድሮስ ሲሳይ ይባላል፡፡
ቴዎድሮስ ከጓደኞቹ
…