በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ለሁለተኛ ጊዜ ተሻሽሏል፡፡
የአሁኑ ማሻሻያ አንድ ድንጋጌን ለማከል የተደረገ ሲሆን በተለያየ ምክንያት ህጋዊ ሰውነቱን ተነጥቆ የነበረን የፖለቲካ ፓርቲ በልዩ ሁኔታ ህጋዊ አድርጎ ዳግም ለመመዝገብ ያስችል ዘንድ ያለመ ነው፡፡
ይህም የሕውሃትን የህጋዊ ሰውነት ይመለስልኝ የሚል ጥያቄ ለመመለስ የተደረገ ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡
ከህግ ሞያ አንፃር የአንድን ተቋም ወይም ግለሰብ ፍላጎት ለማሟላት ህግ ማሻሻል እንዴት ይታያል? ተገቢስ ነው ወይ?
- Category
- Ethiopian News