#Ethiopia #DC #USA #Bringbackourstudents
በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያን የታገቱ የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጉዳይ መንግሥት ለምን ዝም አለ ሲሉ ዛሬ የተቃዉሞ ሰልፍ እያካሄዱ ነዉ።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የታገቱት ተማሪዎች ይለቀቁ፤ መንግሥት ተማሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ ይንገረን፤ ዶ/ር ዐቢይ የት አሉ? ሲሉ ጠይቀዋል። ሰልፈኞቹ ይህን ቁጣቸዉን የገለፁት በዋሽንግተን በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ቅፅር ጊቢ ፊት ነዉ።
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የምናየዉ ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነዉ ያሉት ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የሰልፉ አስተባባሪ ጋዜጠኛ አበበ በለዉ፤ በአሁኑ ሰዓት ከ 24 በላይ የሚሆኑ የደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በአጋቾች ተይዘዉ ፤ የት እንደደረሱ ሳይታወቅ 52 ቀናት ሞልቶዋቸዋል ብለዋል። መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ እያደረገ ያለዉ አንዳችም እንቅስቃሴ መኖሩን በይፋ ለማሳወቅ የተቸገረበት ጊዜ ነዉ፤ በአንድ ወቅት አቶ ንጉሡ ወጥተዉ ተለቀዋል ከማለት በዘለለ ከቤተሰቦቻቸዉ ማገናኘት ያልቻሉበት ሁኔታን ነዉ እያየን ያለዉ ሲሉም አክለዋል።»
- Category
- Ethiopian News