Loading...

በሕወሓት አመራሮች ላይ የደረሰው ውርደት በዘራችሁ አይድረስ ። – ጀነራል ብርሃኑ ጁላ

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

#Ethiopia #ENDF #Tplfisdead #Birhanujula

ጁንታው ለአመታት የተዘጋጀበትን ጦርነት እኛ በሁለት ሳምንት በማጠናቀቃችን አሁን ወንጀለኞችን በማደን ላይ ነን ሲሉ የመከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።
ጀነራል ብርሃኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት ባደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ሰራዊቱን በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ላደረገው ድጋፍና እገዛም አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ጀነራሉ በንግግራቸው የሰሜን እዝ ሰራዊት ለትግራይ ህዝብ ያልከፈለው ዋጋ የለም ብለዋል።
ሰራዊቱ ትግራይ ላይ በመቀመጡ ብቻ በሚያወጣቸው ወጭዎች በየዓመቱ አራት ቢሊዮን ብር ኢንቨስት ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።
ይህን ሁሉ ነገር ሲያደርግ በነበረ እዝ ላይ ጁንታው የፈፀመው ጥቃት የአውሬነት ድርጊት ነው ብለዋል ጀነራል ብርሃኑ።
ጁንታው ያደረሰው ጥቃት አንድ ሆኖ ብቻውን ሲሰራ የነበረውን ወታደር እንደ አስር ግለሰብ እንዲሰራ አድርጎታል ሲሉም ገልጸዋል።
በዚህ ጥቃት የተፈጠረው እልህ፣ ወኔና ቁጭት በሰራዊቱ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የጀግንነት ስሜት እንደፈጠረም ጠቁመዋል።
ጁንታው ለሁለት አመት ሲያደርግ የነበረውን የውጊያ ዝግጅትም እኛ በሁለት ሳምንት ውስጥ በድል አድራጊነት አጠናቀነዋል ብለዋል።

Category
Ethiopian News

Post your comment