Loading...

በተጻራሪ በእውቀት ማነስና በአመለካከት ችግር ከቆሙለት አላማ ውጭ የሚንቀሳቀሱትን ዲፕሎማቶች እናስተካክላለን - ገዱ አንዳርጋቸው

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

በታላቁ ህዳሴ ግድብና በአባይ ወንዝ ፍትሀዊ አጠቃቀም ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሰጡት ማብራሪያ

ኢዜአ - የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በሙሉ ጊዜያቸው እየሰሩ ካሉ ዲፕሎማቶች በተጻራሪ በእውቀት ማነስና በአመለካከት ችግር ከቆሙለት አላማ ውጭ የሚንቀሳቀሱትን የማስተካከል ስራ እንደሚሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ።
-
ሚኒስትሩ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና በአባይ ጉዳይ ከሃገሩ ጎን የማይቆም ዲፕሎማት መኖር የለበትም ብለዋል።
-
አያይዘውም ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ድርድር በገባችበት ወቅት ማንም ሰው ከሃገሩ ጎን መቆም እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።
-
የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች የሃገራቸውን ብሄራዊ ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ ቀንና ሌት እየሰሩ መሆኑንም አንስተዋል።
የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና በአባይ ወንዝ ፍትሃዊ አጠቃቀም ዙሪያ ኢትዮጵያ ያላትን አቋም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ ረገድ ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው እየሰሩ መሆኑንም ጠቁመዋል።
Category
Ethiopian News

Post your comment