“የሚገርመው ዛሬ ልደቴ ነው፡፡ በጥምቀት ነበር የተወለድኩት፡፡”
“የመጨረሻ ጊዜ እዚህ ቦታ የነበርኩት የ16 አመት ልጅ ሳለሁ ነበር፡፡”
አርቲስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ ከአማራ ራዲዮ እና ሁሉም ኤፍ ኤም ጣቢያዎቻችን ላይ በቀጥታ በመግባት አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡
“በትግራይም በአማራ ክልል መካከል በተፈጠሩ ችግሮች የተጎዱ ብዙ ሰዎች ስላሉ የምንረዳዳበትና ለተቸገሩት የምንደርስበት ሰአት ነው፡፡”
ዛሬ በደስታ ብናከብርም በማንነታቸው ሜዳ ላይ የተጣሉ በጣም ብዙ ኢትዮጵያውያን አሉ፤ በቅርቡ በትግራይ በተፈጠረው ችግር ትልቅ የሰብአዊ ቀውስ ተከስቷል፡፡ ከጊዚያዊ ስሜት ወጥተን የምንተሳሰብበት የተቸገሩትን የምንረዳበት አብረን የምንቆምበት ከእልህ፣ቂምና ጥላቻ ወጥተን ዘላቂውን ወደፊት ልጆቻችን የሚኖርባት አገር ስለሆነች በይቅርባይነት በመተው በመፈቃቀድ ይህንን ችግር ማለፍ እና መተሳሰብ አለብን ሲል ለአማራ ራዲዮ ሃሳቡን ሰጥቷል፡፡
በትግራይም በአማራ ክልል መካከል በተፈጠሩ ችግሮች የተጎዱ ብዙ ሰዎች ስላሉ የምንረዳዳበትና ለተቸገሩት የምንደርስበት ሰአት ነው፡፡
- Category
- Ethiopian News