Loading...

የቤንሻንጉል ጉሙዝ አመራር ከሕወሃትና ኦነግ ተልዕኮ ተቀብሎ አማራን እያስጨፈጨፈ የሐሰት መረጃዎችን እያሰራጨ ነው የአማራ ክልል ሰላምና ደሕንነት ግንባታ ቢሮ

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

"ጥቃቱን የፈፀመው የቀበሌ አመራር የራሱን ጎሳ አደራጅቶ ነው፣ የአማራና የአገው ሕዝብን እያጠቃ ያለው የቤንሻንጉል አመራር ነው"
-
መተከል ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ኮሙኒኬሽን እንዲሁም የመንግስት ሚዲያዎች በግለሰብ ግጭት የተከሰተ ነው ብለው በተጨፈጨፉት ላይ የሀሰት ዜና ሰርተውበታል። ይሁንና የአማራ ክልል ሰላምና ደሕንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊው አቶ ሲሳይ ዳምጤ በግለሰብ ግጭት የተባለው ውሸት መሆኑን ተናግረዋል።
-
ጭፍጨፋው የተፈፀመው ወንድሙ የተጠቃበት (ማን እንዳጠቃው አልታወቀም) የቀበሌ ኃላፊ የራሱን ጎሳ አደራጅቶ መሆኑን በግልፅ ተናግረዋል። የቤንሻንጉል ጉሙዝ አመራር ከትህነግና ኦነግ ተልዕኮ ተቀብሎ አማራን እያስጨፈጨፈ እንደሆነም በግምገማ እንደታመነ ተናግረዋል። አማራና አገውን እያጠቃ ያለው የቤንሻንጉል አመራር ነው ብለዋል። ሰውዬው ያረጋገጡት ፌስቡከኛው ሲጮኸው የሰነበተውን ጉዳይ ነው።

ነገር ግን:_

የግለሰብ ፀብ ነው ብሎ በሀሰት ዜና ሲያሰራ የነበረው የቤንሻንጉል ሰላምና ደሕንነት ኃላፊ ነው። ይህን የሀሰት ዜና የሰራው የመንግስት ሚዲያ ነው። በጭፍጨፋ ላይ እንዲህ እየቀለዱ እንዴት ዝም ይባላሉ?

አመራሩ ነው እያጠቃ ያለው እየተባለ አሁንም ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ ሲቀየርላቸው እንደለውጥ እየታየ ይቀጠላል?

የቤምሻንጉል ጉሙዝ አመራር ይህን እያደረገ የአማራን ክልል የፀጥታ ኃይል የሚመሩት እነ ሲሳይ አስተያየት እየሰጡ ነው የሚቀጥሉት?

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት አጥቂ በሆነበት፣ የፌደራል መንግስቱ ትኩረት ባልሰጠበት የአማራ ክልል መንግስት ግቡ ከተባልን እንገባለም እያለ ነው የሚቀጥለው?

እውነታውን መናገራቸው መልካም ሆኖ፣ የአማራ ክልል አመራር እንዲህ እንደ ግለሰብ ስለጉዳቱ እየተናገረ ነው የሚቀጥለው?

ሰሞኑን ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ ሲባል የከረመውን መልሰው እያረጋገጡ ነው። አሁንም ፌስቡክ ላይ ጥቃት የሚያስፈፅም አመራር ጥቆማ እየተደረገ ነው። የአማራ ክልል አመራር ይህን የሚሰማው ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ ነው?

Category
Ethiopian News

Post your comment