Loading...

በለቅሶ መዘዝ ለኮሮና ቫይረስ ተጋልጠዋል ተብለው የተጠረጠሩ ከአከባቢያቸው እንዳይወጡ የተደረጉት የአብነት አከባቢ ነዋሪዎች (Video)

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

Ethiopia : Coronavirus Lock Down in Addis Ababa , Abinet Area (DW Video)
የለቅሶዉ መዘዝ
አዲስ አበባ ዉስጥ በልደታ ክፍለ ከተማ፣ በወረዳ 3 ፣ ቀጠና 5 ፣ መንደር 3 (በተለምዶ አብነት የሚባለው አካባቢ) የኮሮና ተሕዋሲ በርካታ ሰዎችን በመልከፉ ወይም በመያዙ ምክንያት የአካባቢዉ ነዋሪዎች በሙሉ ከሌሎች አካባቢዎች ነዋሪዎች ጋር እንዳይገናኙ ታገዱ።እርምጃዉ የተወሰደዉ በነዋሪዎቹ ፈቃድና ይሁንታ ነዉ ተብሏል።የመንደሩ ነዋሪዎች ከወትሮ እንቅስቃሴቸዉ እንዲታቀቡ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ ፖሊስ ጠንካራ ቁጥጥር እያደረገ ነዉ።
በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችም ይህንን ስራ እያስተባበሩ መሆኑን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ተመልክቷል።ኢትዮጵያ ዉስጥ በኮቪድ 19 የሞቱት የ4ኛው ሰው ቤተሰቦችን ለማስተዛዘን ለቅሶ ተቀምጠው የነበሩ ከ30 በላይ የመንደሩ ነዋሪዎች በኮሮና በተኅዋሲ መያዛቸዉን እርምጃዉን ከሚያስተባብሩ ወጣቶች አንዱ ገልጿል።መንደር 3 አንድ መቶ ያህል መኖሪያ ቤቶች ይገኛሉ ተብሎ ተገምቷል።ቪዲዮ በሰለሞን ሙጬ

Category
Ethiopian News

Post your comment