አዉሎ ሚዲያ – የኦፌኮ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በኦሮሚያ የመንግስት ባለስልጣናት በዜጎች ላይ ከፍተኛ እስራትና ወከባ እየፈጠሩ ነው ሲሉም ተናግረዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የገቡትን ቃል ለማክበር አቅምና ለዚህ አጋዥ የሆኑ የተቋማት ግንባታ የላቸውም በማለት ጨምረው ተናግረዋል።በተለይም አዲሱ የብልፅግና ፓርቲ ሀገሪቱን የማሸጋገር እና የጋራ መግባባት የመፍጠር አቅም የለውም፤ በዚህም ምክንያት ደርግ ሲያደርግ የነበረውን አፈናና እንግልት እየተገበሩ ይገኛሉ ብለዋል። ከአውሎ ሚዲያ ፓርቲያቸው ኦፌኮና እርሳቸው በኦሮሚያ በታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ለምን ዝም አሉ የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ፕሮፌሰር መረራ ጉዳዩ ግራ የሚያጋባና መረጃ ለማግኘትም አዳጋች ሆኖብናል ብለዋል።እንኳን እኛ ግለሰቦች በተማሪዎች ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እራሳቸው መረጃ እንደሌላቸው ተረድተናል በማለትም ተናግረዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፓርቲያቸውን ወክለው የሚንቀሳቀሱ እሳቸውና ደጋፊዎቻቸው በሚዪደርጓቸው ንግግሮች ላይ በርካት ኢትዮጵያውያ ቅሬታ እያቀረቡ ነው በሚል ለቀረበመቸው ጥያቄም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንዳለው የተጋነነ ነገር አላደርግሁም ሁላችንም ኢትዮያዊያን ስለሆንን መገፋፋት አይጠበቅብንም ሲሉም ተናግረዋል።ፕሮፌሰር መረራ ሀገራዊ መግባባትና ብሔራዊ እርቅ ካልተደረገ የነገዋ ኢትዮጵያ ከትላንቷ እና ከዛሬዋ የባሰ ምስቅልቅል ይገጥማታል ብለዋል።
- Category
- Ethiopian News